Thursday, April 7, 2016

❖የተባረከው ተስፋችን

የተባረከው ተስፋችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ወደ ምድር ሲወርድ ተሞልቶ የመጣው ነገር ቢኖር ጸጋንና እውነትን ነው ዮሐ 1:14።ጌታ ከሰማይ ይዞት የመጣው ጸጋ አንድ የሚያድን ሁለት ደግሞ የሚረዳ ጸጋ ነው። በዚህ ጸጋ ፊት ቀርቦ ይቅር የማይባል ኃጢአት የለም። በዓለም ላይ ዋና የተባለው ኃጢአተኛ የተቀበለ እና ለጠላት ምህረት ያረገ ጸጋው ነው።
ምንአልባት ዛሬ ከኃጢአተኝኘታችን የተነሳ ሥጋችን ተፀይፈን ፣እኛነታችንን ጠልተን የምንኖር ልንሆን እንችላለን። እኔን እግዚአብሔር ይቅር አይለኝም የሚል የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ያለን ባዶነት የሚሰማን፣ የበደል ሸክም የከበደን የኃጢአት ሞራ አይናችን ጋርዶን መሪ እንዳጣ ሰው እጃችንን ዘርግተን ብንዳብስ የምንይዘው አተን ዙርያው ሁሉ ጨለማ ሆኖብን ተቸግረን ይሆናል። በዚህ ውስጥ ካለን ዛሬ ግን እኛ የሚጠበቀው ነገር ቢኖር ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ " ዕብ 4:16
በዚህ ጸጋ ዙፋን ፊት የበደለ ይማራል፣ የደከመ ይበረታል፣ ያዘነ ይጽናናል። በእግዚአብሔር ዘንድ ለሁሉም የሚበቃ የትኛውንም ኃጢአት ይቅር የሚል የጸጋ ባለጸግነት አለ። ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል ቲቶ 2:11-13
ከሞት ያዳነን ይህ ጸጋ ሦስት ነገርን ያስተምረናል።
1, ኃጢአተኝነትንና አለማዊ ምኞትን መካድ።
2, የተባረከውን ተስፋችንን መጠበቅ
3, ራሳችንን በመግዛት በጽድቅ እግዚአብሔርን በመምሰል መኖር ነው።
የተባረከ ተስፋ የተባለው የታላቁ የአምላካችንና የመዳኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር መገለጥ ነው። ጌታ ኢየሱስ ከነገረን ተስፋ መካከል አንዱ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ ዮሐ 14:3
ክርስቲያኖች የምንጾናናበት ቃል አንዱ ጌታ ክፉ ከሆነው ከአሁኑ አለም ሊያድን ይመጣል የሚል ነው። እኛ እኮ ወዳጆቼ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች አይደለንም ከሰማይ ሊያድነን የሚመጣውን ጌታ የምንጠባበቅ የተባረከ ተስፋ ያለን ነን ስሙ ይባረክ። ጌታ ኢየሱስ እኛን ለመውሰድ በትዕዛዝ በመላእክት አለቃ ድምፅ ከሰማይ እስከ አየር ድረስ ሲወርድ በመጀመሪያ በክርስቶስ የሞቱ ይነሳሉ ከዚያ በኃላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ከእነርሱ ( ከሞት ከተነሱት ) ጋር በደመና እንነጠቃለን 1ተሰ 4:13-18
ከመነጠቃችን በፊት እኛ ሕያዋን የሆነው እንለወጣለን ሙታን ደግሞ የማይበሰብሱ ሆነው ይነሳሉ 1ቆሮ 15:52 ይህ የክርስቲያኖች ንጥቀት ከክርስቶስ ጋር መሰወር ተብሎ ተገልጾአል። ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና ቆላ 3:3
እኛ ከክርስቶስ ጋር ተሰውረን የምንቀር ብቻ አይደለንም ክርስቶስ በክብር በሚገለጥበት ጊዜ ክእርሱ ጋራ የምንገለጥ ነን። " ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ" ቆላ 3:4
የተባረከው ተስፋችን በመጀመሪያ ለቅዱሳኑ ሲመጣ የተነጠቅነው ወይም ከእርሱ ጋራ የተሰወርነው እኛ ከቅዱሳኑ ጋር ሲመጣ ደግሞ ከእርሱ ጋራ በክብር እንገለጣለን እርሱ ሲነግስ አብረን እንነግሳለን። አሜን።
             ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሔር  ሁን አሜን።


❖ዘንዶውን በኒውክሌር እናግዛለን፤አምላክንም እናሸንፋለን

‹‹ዘንዶውን በኒውክሌር እናግዛለን፤አምላክንም እናሸንፋለን!››

የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ
ሁሉም ኢትዮጵያዊ አቅልሎ ያየው፤ነገር ግን እጅግ ከባድና ትኩረት ልንሰጠው የሚገባን ነጥብ ነበር፡፡
ኢትዮጵያን አቅልለንና ንቀን የምናያት እኛ ዜጓቿ ብቻ ነን፡፡በአሁኑ ሰዓት ግን ይህ ራስን የመናቅ አባዜ ማክተም ያለበት ይመስላል፡፡
ወደደድንም ጠላንም፣አመንንም አላመንንም፣አማኝም ሆንን ኢኣማኒ ይቺ ዓለም መጥፋቷ አይቀርም፡፡መጥፊያዋ ደግሞ ተቃርቧል፡፡
በትንቢቱም ይሁን በሳይንስ፤አሊያም በአየር ብክለት ወይም በሌላ የተፈጥሮ አደጋ ዓለም ልትጠፋ ብትችል የሰውን ልጅ ላያሳስበው ይችላል፡፡
ይህን የዓለም ጥፋት ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ ስናመጣው ግን መልኩን ይቀይራል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም መነሻ ነበረች፤አሁንም የዓለም መጨረሻና መደምደሚያ መሆኗ ገሀድ እየሆነ ነው፡፡ይህንን እኛ ኢትዮጵያውያውያን አናምንም፤አንቀበልም፡፡ሌላው ዓለም ግን አምኗል ተቀብሏል፡፡
በቅርቡ ማለትም በኛ አቆጣጠር በ 2007 ዓ.ም አጋማሽ ፍስሐ ያዜ ካሳ በተባለ ጋዜጠኛና ደራሲ የተፃፈ መፅሀፍ ነበር፡፡ርዕሱ ‹‹የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ›› ይሰኛል፡፡ይህ መፅሐፍ ምንም እንኳን ለደራሲው መጥፊያው ቢሆንም አገኘሁ ያለውን እውነት ለኢትዮጵያውያን ሊያሳይበት ሞክሯል፡፡
የዚህ መፅሐፍ ትኩረት ስለ አዲሱ የምድር መንግስት ምስረታ ብቻ አይደለም፡፡የፍፃሜው ጦርነት ምን እንደሚመስል፣ኢትዮጵያም ከፍፃሜው ጦርነት ጋት በተያያዘ የተለየ ትኩረት እንደተደረገባት፣‹‹ዘንዶውን በኒውክሌር እናግዛለን፤እግዚአብሔርንና መላዕክቱንም እናሸንፋለን›› ብለው የኃያላን አገራት መሪዎችና የቫቲካን ቤተክርስቲያን የሚዝቱበትና የሚዘጋጁበት፤ ጦርነቱም በዋናነት ኢትዮጵያ ላይ እንደሚሆን፤ጎላቸውም ኢትዮጵያ እንደሆነች ይገልፃል፡፡የዓለማችን ታላላቅ የሚባሉ አገራትና መሪዎች ከዚህ በኋላ ትልቁ የቤት ስራቸው ኢትዮጵያ ላይ እንደሆነ በማስረጃ እያስደገፈ ተንትኖታል፡፡
ይህ መፅሀፍ በአሁኑ ጊዜ በብዙሃኑ ዘንድ እየተነበበ ያለ ቢሆንም፤በጥቂቶች ዘንድ እንደ ልብ ወለድ እየተቆጠረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ነገር ግን ይህ መፅሀፍ ከተፃፈ በኋላና ለህትመት በቅቶ ወደ አንባቢው መድረስ በጀመረ ማግስት የተፃፉት ነገሮች አንድ ባንድ እየተተገበሩ መጡ፡፡
ፀሐፊው የ G 20 አገራትና የ G 8 አገራት መሪዎች ስብሰባ በሙሉ ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ መሆኑን እየገለፀ ቃል በቃል የዝግ ጉባዔያቸውን ጭብጥ እንደወረደ አስፍሮታል፡፡በፍስሐ አባባል መረጃው የወጣው ከኋይት ሀውስ ነው፡፡
በዋናነት የሚፈልጉት የጣና ሐይቅን አካባቢ ቢሆንም ሙሉ ኢትዮጵያ ዋና ጎላቸው ናት፡፡በዚህ መሰረት የጣና ሐይቅ ምንነቱ ባልታወቀ እንግዳ አረም ከመሸፈን ጀምሮ እስከ አቡነ ማቲያስ ወደ ቫቲካን መጓዝ ድረስ በርካታ ነገሮችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ሆኖም ነገሩን ለማሳጠርና በመፅሐፉ የተባሉት ነገሮች ፈጥነው እየተተገበሩ እንዳሉ ለማሳየት የተወሰኑትን ብቻ ልጥቀስ፡፡
መፅሐፉ በ2007 ዓ.ም ለህትመት በበቃ ማግስት ለምሳሌ፤
1. የዓለማችን ቢሊየነር ቢልጌትስ/የስሙ ትርጉም 666 ነው/በቫቲካኑ ጳጳስ እና በአሜሪካ መንግስት አዛዥነት ረቀቅ ባለ ዘዴ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ እንደሚወዳጅና የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጡት ያትታል፡፡ወዲያውም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ዶክትሬቱን ወሰደ፡፡ብዙ የሰራላት አገሩ አሜሪካ እንኳ ያልሰጠችውን ዶክትሬት እኛ ሰጠነው፡፡ይህ ሊሆን የቻለው ቢልጌትስ ወደ ፊት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በኢትዮጵያ በመመደብ ኢትዮጵያዊ ህፃናትንና ሌሎችን በተለይም በገጠራማው ክፍል ያሉትን ማህበረሰቦች የአስተሳሰብ አድማሳቸውን ለማስፋት በሚልና በልማት ስም/በትምህርት፣በጤና፣ በውሃ፣…ወዘተ/በሚል መድሃኒት እየሰጡ ቀስ በቀስ አስተሳሰባቸውን ለማጥፋት እንዲመች ሲባል ለተነደፈው ዕቅድ ነው፡፡
2. ሁሉም የኃላን አገራት መሪዎች/የ666 ዓባላት/በጳጳሱ በአቡነ ፍራንሲስ አዛዥነት ወደ ኢትዮጵያ መሄድ እንዳለባቸውና የባፎሚትን፤በፍስሀ አገላለፅ የዘንዶውን፣በመፅሐፍ ቅዱስ አገላለፅ የአውሬውን፣በተከታዮቹ አገላለፅ የሉሱፌልን፣በጥቅሉ የሳጥናኤልን ዓላማ ለማሳካትና ኢትዮጵያ ላይ ለሚኖረው መንፈሳዊ የፍፃሜ ጦርነት ዝግጅት ሲባል እንዲያጠምቁዋቸው መታዘዛቸውን አንብበን ነበር፡፡ይህን በፍስሐ መፅሀፍ ባነበብን ማግስት ደግሞ ባራክ ኦባማ ወደ ኢትዮጵያና ወደ ሌላው የምስራቅ አፍሪካ አገራት መጣ፡፡መጥቶም ስለ ወንድ ለወንድ ጋብቻ ነፃነትና ስለሌላው ነገር ደስኩሮ ሄደ፡፡
3. ከቆይታ በኋላ ደግሞ ታስቦም ታልሞም በማያውቅ መንገድ በቀጥታ ከዘንዶው መልዕክት ተቀብለው ለኃያላን አገራት መሪዎችና ለዓለም የሐይማኖት አባቶች ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት ራሳቸው አቡነ ፍራንሲስ ወደ ኬንያና ውጋንዳ፣ቀጥሎ ወደ መካከለኛው አፍሪካ መጡ፡፡ቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ቢመጡ ከፍተኛ ቁጣ እንደሚነሳባቸው ስለሚውቁ ወደ ጎረቤት አገር ሄደው የተንኮል ችግኛቸውን ተክለው ተመለሱ፡፡እንደተመለሱ ደግሞ የኛውን ጳጳስ አቡነ ማቲያስን ወደ ቫቲካን አስጠርተው አነጋገሩ፡፡የግብፁ አቡንም ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውና በመስቀል አደባባይ ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
4.በተመሳሳይ ሁኔታና ለተመሳሳይ አጀንዳም የቀድሞው የአሜሪካ መሪ ቡሽ በድብቅ መጥቶ ላሊበላንና ሌሎችን ቦታዎች ጎብኝቶ ሾልኮ ሊሄድ ሲል ሚስጥሩ ወጣና ይፋዊ ዜና ሆነ፡፡ተደብቆ መምጣቱ ለምን እንዳስፈለገም አልታወቀምና ብዙዎችን ግራ አጋባ፡፡
5.የቻይና፣የጃፓን፣የቱርክና የሌሎች የG20 አባል አገራት በተካካይ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውና፤ለህንድና ለሌሎች አገራት የብሄር ግጭትን የፈጠሩ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች መሰጠት፣የጃፓን ግዙፍ የንግድና የገንዘብ ተቁዋም መመስረት፣በመቶ ኪሎ ሜትር ካሬ የሚገመት ቦታ ለጅቡቲ ውሃ ማውጫ በሚል ከኢትዮጵያ መሬት ላይ ተቆርሶ ለ 30 ዓመት ለጅቡቲ መሸጡ፣ሶቨሪ ቦንድ በፓርላማ ጸድቆ ተግባራዊ መሆኑና ወዘተ..የተባሉት ነገሮች ወደ ተግባር ፈጥነው እየተለወጡ ለመሆናቸው አመላካች ነው።
6. በቅርቡ ደግሞ በመፅሃፉ እንደተገለፀው የኢጣሊያው መሪ ባልተለመደ ሁኔታ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ረጅም በሚባል መልኩ 5 ቀናትን አሳለፈ፤ላሊበላንም ሌላውንም ጎበኘ…፡፡
(በነገራችን ላይ እነዚህን ገጠመኞችና መምጣት መሄዶችን እንደ ተራ ክስተተት ወይም ገጠመኝ የማናይበት ምክንያት በመፅሐፉ ውስጥ በተገለፀው መሰረትና በፕሮግራማቸው መሰረት የተከናወኑ በመሆናቸው ነው፡፡
የእያንዳንዱ አገር መሪ ጎላቸው ኢትዮጵያ እንደሆነች የተገለፀላቸው በ 2014ቱ የ G 20 ስብሰባ ላይ ነው፡፡በጳጳሱ በአቡነ ፍራንሲስ ሰብሳቢነት ሲነጋገሩባትና በዝግ ስብሰባቸው ላይ ስለ ኢትዮጵያ ሲያነሱ፤መሪዎቹ እየተገረሙና እየተደነቁ ያነሱዋቸውን ጥያቄዎችና መልሶች መፅሐፉ ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡በፍጥነትና በተከታታይ ወደ ኢትዮጵያ መሄድ እንዳለባቸውም የታዘዙት በዚሁ ጉባኤ ላይ ነው፡፡)
7.ቀጥሎ ደግሞ በመፅሐፉ በተገለፀው መሰረት ከሳምንታት በፊት የኢትዮጵያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቲያስ ወደ ሮም ተጓዙ፡፡ተጉዘው ሽልማትም ተሰጥቶዋቸው መጡ፡፡ዝቅ ብላችሁ ምስሉን እንደምታዩት ከ አቡነ ፍራንሲስ ጋር ተሳስመው፣ተነጋግረው በኢትዮጵያውያን ምዕመንም ተሳልቀው መጡ!
8.ታስታውሱ እንደሆነ በሚሊኒየማችን ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ወጣት ኢትዮጵያዊ ለማጥመድ ትጠቅማለች ተብላ የተላከችው ቢዮንሴ የተባለችው ዘፋኝ(አሁን አምላክ ሆና፤የራሱዋን ቤተ ክርስቲያን መስርታ፤የራሱዋን መፅሐፍ ቅዱስ አፅፋ እየተመለከች ነው)መጥታ በአደባባይ የኢትዮጵያን ህፃናት ሰብስባ ባፎሚትን አስመልካ እንደሄደችው ሁሉ፤አሁንም ሰፊውን የኢትዮጵያ ወጣት ክፍል ለማጥመድ ሌላ ዘዴ ተፈለገ፡፡ ኢትዮጵያውያውያን ወጣቶች የተወሰዱበት ኳስ ሆኖ ስለተገኘም እነሱን ለማጥመድ በኳስ ዙሪያ ኢትዮጵያ ላይ መሰረት ተጣለ፡፡የዚህ ከፍተኛ ኃላፊነትም በፊፋ ላይ ወደቀ፡፡ስለዚህ በሴፍ ብላተር የተተኩት አዲሱ የፊፋው ፕሬዘዳንት በተመረጡ ማግስት የመጀመሪያ ስራቸው ያደረጉት ወደ ኢትዮጵያ መምጣትና መጎብኘት ነበር፡፡ከሶስት ቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ጎብኝተው ሄዱ፡፡ኢትዮጵያ ታሪካዊ አገር ስለሆነች መጎብኘት ፈልገው አይደለም፡፡ያ ቢሆን ከመመረጣቸው በፊት ሰፊ ጊዜ ነበራቸው፡፡ወይም ከተመረጡ በኋላ ሌሎች ስራዎቻቸውን አስቀድመው ተረጋግተው መጎብኘት ይችሉ ነበር፡፡የመምጣታቸው ዓላማ ሌላ ስለሆነ ግን በኳስ መቃብር አገር በኢትዮጵያ ፈጥነው ተገኙ፡፡
9.ይህ ከመሆኑ ከጥቂት ጊዜ በፊት ደግሞ ሴፍ ብላተር በወረዱ ማግስት አዝናኝና ዲፕሎማሲያዊ አቀራረብ ባለው መንገድ ለስለስ ተደርጎ አንድ ዜና ተነገረን፡፡ዳሽን ቢራ ምንም በማይገናኝና በማይመስል መንገድ ከአርሰናል ጋር የረጅም ዓመት የምናምን ውል አደረጉ፡፡…ወዘተ…ተብሎ በበጎ ጎኑ የታየ ዜና ተነገረን፡፡እንዴት ኢትዮጵያን?እያለ የሚጠይቅ ካለ ምላሹን በቀላሉ ማግኘት ይችላል፡፡
10.ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደግሞ ዓለምን በአንድ በአውሬው /በ666/ አገዛዝ ስር ለማስገዛት የሚታትሩት የሃያላን አገራት መሪዎችና የቫቲካን ቤተክርስቲያን እንቅፋት የሆነችባቸው ብቸኛ አገር ሶሻሊስቷ ኩባ ነበረችና ባልተለመደ ሁኔታ በመጀመሪያ ጳጳሱ ፍራንሲስ ወደ ኩባ ተጉዘው ኩባን ጎበኙ፡፡ቀጥሎ ደግሞ ዓለምን ባስገረመ መንገድ ኦባማ ራሱ ወደ ኩባ ሄዶ ለማሳመን ሞከረ፡፡ከሽብርተኝነት ሊስት አውጥተናችኋል አሏቸው፡፡ለ90 ዓመታት አደገኛ ጠላት ሆነው የቆዩ ነበሩ፡፡ባሁኑ ሰዓት የ 666 ማይክሮ ችፕ (የአውሬው ምልክት)በአገሬ ህዝብ ላይ አይገጠምበትም ብሎ የሚዝተው ብቸኛው ሰው አዛውንቱ ፊደል ካስትሮ ብቻ ነው፡፡ቢሆንም የአገሪቱ ፕሬዘዳንት የፊደል ካስትሮ ወንድም ራውል ካስትሮ ለዘብ ሊልላቸው ሞክሮዋል፡፡ሁለቱ ባይስማሙ እንኳን እድሜያቸው ስለገፋና በቅርቡ መሞታቸው ስለማይቀር፤ዋናው ህዝቡን ማሳመን ነውና ጳጳሱ በኩባ ጉብኝታቸው ከፍተኛውን የካቶሊክ እምነት ተከታይ ቀልብ መግዛት ችለው ነው የተመለሱት፡፡
ይህ ሁሉ ነገር በገጠመኝ እንዳልሆነ ብቻ ሳይሆን፤ለምን እንደሚሆንና መቸ እንደሚሆን ቀድሞ የነገረን ፍስሐ ያዜ ነው፡፡በዚህ ድንቅ መፅሐፍ ውስጥ የአቡነ ፍራንሲስና የኃያላን አገራት መሪዎች ሴራ በደንብ ተተንትኗል፡፡የዘመኑ ስሌትና ቀመርም እንዲሁ፡፡ይህ ሁሉ ውጣ ውረድ ዓለምንና ህዝቦቿን በረቂቅ ቴክኖለጂ አጋዥነት ጠቅልሎ በአንድ በሳጥናኤል አገዛዝ ስር ለማድረግ ሲባል ነው፡፡ለዚህም ሁሉም በየፊናው ተሰማርቶ ይገኛል፡፡የአገር መሪ፣የሐይማኖት መሪ፣የሙዚቃው ኢንደስትሪ መሪ…ከፍተኛ የገንዘብ አቅምና በቢሊዮን የሚቆጠር ተከታይ ያለው የእንግሊዝ ኳስ፣ወዘተ…!የሁሉም ትኩረት ደግሞ ኢትዮጵያ!ናት፡፡
ለምሳሌ ቢዮንሴ የተባለችው ዘፋኝ በሚሊኒየማችን ወቅት መጥታ በአቡነ ጳውሎስ አማካኝነትና መልካም ፈቃድ ወደ ቤተ መቅደሳችን ገብታለች፡፡ያውም ከነጫማዋ፡፡ ስትጨፍር አድራ በሚኒስከርትና በሂል ጫማ ሆና፤በከበሮ፣በፀናፅልና በወርቅ ጥላ ታጅባ ነው በቤተ መቅደስ አቀባበል የተደረገላት፡፡በዚያ ወቅት በእርዳታ ልብስ ጀቡና የባፎሚትን ፅላት ተክላ መሄዷ እንዳለ ሆኖ፤አሁን ደግሞ the national church of bey በሚል ቤተክርስቲያን መስርታ አምላክ ሆና እየተመለከች ነው፡፡bible የሚለውንም beyble በሚል ቀይራ የራሱዋን ባይብል እያሳተመች ነው፡፡ዝቅ ስትሉ ምስሉ ላይ እንደምታዩት ቢዮንሴ እግዚአብሔርን ተክታ እየተመለከች ነው፡፡
ዓለም ይህን ሁሉ ነገር እያነሳ ሲጥል የኛው ድንቅ ደራሲ ግን ቀድሞ ሁሉንም ነገር ነግሮን ነበር፡፡ያውም በሚገባን መንገድና በሚገባን ቋንቋ!
ፍስሐ ያዜ ‹‹የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ›› በሚለው መፅሀፉ ከአዳም በፊት ከነበሩት ፍጥረቶች ጀምሮ እስካሁኑ ዘመን ድረስ ምን ምን እንደተከናወነና ያ ሁሉ ክንውንም ኢትዮጵያን ከማጥመድ ጋር የተያያዘ እንደነበር በማስረጃ እያስደገፈ ይነግረናል፡፡ወደ ፊት ምን እንደሚከሰትም እንዲሁ፡፡
የቫቲካኑ ጳጳስ ብዙ ግፍ የፈጸሙ ከመሆናቸውም በላይ በ100ሺ ህፃናት መስዋዕትነት የተከሰሱ ናቸው፡፡ህፃናትን እየሰው ሳጥናኤልን ያገለግላሉ፡፡የቫቲካን ቤተክርስቲያንግብረ ሰዶማውያንን የፈቀደች ናት።ጳጳሱም ቆመው በክብር እያጋቡዋቸው ይገኛሉ።የመጽሀፍ ቅዱሱ ሰድምና ገመራ በነሱ ዘንድ ሀጢያት መሆኑ ቀርቶ እንደ ትልቅ መባረክ ተቆጥሮዋል።በ june 2015 ደግሞ በቫቲካን የሀይማኖት መሪዎችን ሰብስበው አምላክ በሙሴ 10ቱ ትዕዛዛት ላይ 2 ጨንሮልናል በማለት ሁሉም ሰው ማይክሮ ችፑን በጸጋ እንዲቀበልና የጾታ እኩልነት ገደብ ሳይጣልበት የወንድ ለወንድ ጋብቻ የተቀደሰ እንደሆነ በምግለጽ አስጨብጭበዋል።ስበመፅሐፉ ውስጥም ግብረሰዶማዊ ከሆነው ከኦባማ ጋር በስብሰባው መድረክ ላይ ሆነው ሲዳሩ ይታያል፡፡የኦባማ ሚስትም ወንድ መሆኗና ልጆቹም በአንጀሊና ጆሊ አማካኝነት ከኢትዮጵያ በማደጎ የተወሰዱ እንደሆኑ ወዘተ….በመፅሐፉ ይተረካል፡፡
‹‹ነገር ግን…››ይላል ፍስሐ በመፅሃፉ ብዙ ከነገረን በኋላ፤‹‹ነገር ግን….ኢትዮጵያውያን ነጭ አምላኪ ስለሆንን በአማርኛ ስለተፃፈና በኢትዮጵያዊ ፀሀፊ ስለተፃፈ ወይም ነጭ ስላልፃፈው ብቻ ኢትዮጵያውያን አይቀበሉትም!ስለዚህ ይህን መረጃ በሙሉ በነጭ በኩል ማውጣት ብቸኛ አማራጭ ነው!››በማለት በቁጭት ይነግረናል፡፡ለዚህም ይመስላል መፅሐፉ January 2016 ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው፡፡በቅርቡ ይህን የፍስሐ ያዜን መፅሐፍ በአትላንታ የሚገኝ አንድ ክርስቲያናዊ ተቋም ወደ እንግሊዝኛ ተርጉሞ በማሳተም ለንባብ አብቅቶታል፡፡‹‹the goal of satan›› በሚል ርዕስ ነው የተተረጎመው፡፡ምናልባትም ዘ ጎል ኦፍ ሳታን ላይ የቫቲካኑ ጳጳስ ሴራቸውና ጸረ ኢትዮጵያነታቸው ስለተገለፀባቸው ይመስላል በስደተኞች አሳበው አንድ ነገር ፈጥነው አደረጉ፡፡ትሁትነታቸውን ለማሳየት ብለው በአውሮፓ የሚገኙትን ስደተኞች እግር የማጠብ ፕሮግራም ያዙና የኢትዮጵያውያንንና የኤርትራውያንን እግር አጥበው መሳም ጀመሩ፡፡ይህ ተግባራቸውም በዓለም ሚዲያ ተሰራጨላቸው፡፡ምስሉን ዝቅ ብላችሁ መመልከት ትችላላችሁ፡፡
በነገራችን ላይ ቀደም ብሎ የተሰራ አንድ ተከታታይ ፊልም ነበር።አሁን በታዋቂ ቻናሎች እየታየ ነው፡፡የዓረብ ቻናል ተጠቃሚዎች ካላችሁ በቀላሉ አክሽን ላይ መከታተተል ትችላላችሁ፡፡የፊልሙ ርዕስ sleepy hollow ይሰኛል፡፡ይህ ፊልም ከሚያነሳቸው ጭብጦች ውስጥ አንዱ፤በግእዝ ስለተፃፉ ጥንታዊ የኢትዮጵያ መፃህፍት ሲሆን፤ በዋናነት ስለ ‹‹መርበብተ ሰለሞን››ይተርካል፡፡መርበብተ ሰለሞን ደግሞ ከግዕዝ ወደ ሁሉም የዓለም ቋንቋዎች ተተርጉሞ በሚስጥራዊ አባላት ዘንድ በደንብ የተፈተሸና አስፈላጊነቱ የታመነበት መፅሐፍ ነው፡፡እኛ ደግሞ በግእዝ ስለተፃፈ ብቻ ሚስጥሩ ሳይገባንና ንቀነው ሁሉንም ሰነድ ተረት ተረት ብለነዋል፡፡ የሚገርመው ግን በፍስሐ መፅሐፍ ውስጥ ሁሉም የኃያላን አገራት መሪዎችና የቫቲካኑ ጳጳስ ግእዝ ተናጋሪዎች እንደሆኑና፤ከዘንዶው በተሰጣቸው ጥበብ ተጠቅመው በግእዝ ለልዑላቸው ለሳጥናኤል ቅኔ እንደሚዘርፉ፤አጠቃላይ የውጊያቸው ቀመር የግእዙን ሰነድ ተንተርሶ እንደሆነ በደንብ ይብራራል፡፡ስለ መፅሐፈ ሄኖክም ብዙ የሚለው አለ፡፡
ስለ ፍስሐ ያዜ መፅሀፍ በዚህ አጭር ገፅ አውርቶ መጨረስ አይቻልም፡፡ ብቻ ግን ‹‹የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ›› የሚለውን መፅሐፍ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንዲያነበው መጠቆም እፈልጋለሁ፡፡ይህን ፅሁፍም ለቁም ነገረኛ አንባቢያን ሼር እንድታደርጉት እመክራለሁ፡፡ቢያንስ ቢያንስ በዙሪያችን ምን እየተከናወነ እንዳለ ባናውቅ እንኳን ምን እያንዣበበብን እንዳለ ማወቁ ጠቃሚ እንጂ ጎጅ ነገር የለበትም፡፡
አንድ ነገር ልጨምር፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የቫቲካኑ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቲያስ ወዳጅነታቸውን በዓለም ፊት አውጀዋል፡፡የቫቲካን ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የኢትዮጵያን ውድቀት የሚሹ ከመሆናቸውም በላይ፤በቀጥታና በተዛዋሪ በአገሪቱና በሐይማኖተኛው ላይ ከፍተኛ ጥፋት ፈፅመዋል፡፡ጨርሶ ወዳጅነት የሚባል ነገርም የለም!በሞሶሎኒ ዘመን እንኳ የኢጣሊያን ታንክ ባርከው፣ሰራዊቱን መርቀው ‹‹ኢትዮጵያን ውረሩ፤ሰውንም አገሩንም በመርዝ ጋዝ አጥፉ!››ብለው ከመሸኘታቸውም በላይ፤የቤተክርስቲያኒቱን የወርቅ መስቀል ለጦርነቱ እንዲያውሉት በስጦታ ሰጥተዋል፡፡ከዚያ ዘመን ጀምሮም የቫቲካን ቤተክርስቲያንና ጳጳሳቱ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያንና ህዝቡን፤እንዲሁም ኢትዮጵያን ይቅርታ እንዲጠይቁ ብዙ ጊዜ በሐይማኖት አባቶችና በምሁራን ተለምነው አሻፈረን ያሉ ናቸው፡፡ዛሬ ግን ከኋላ የመጣ ዓይን አወጣ እንዲሉ አቡነ ማቲያስ ወደ ቫቲካን ተጉዘው፤የዶለቱትን ዶልተው፤ሽልማታቸውንም ተቀብለው፤እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤‹‹ከቫቲካን ጋር ፍቅር ነበርን፡፡የነበረንን የቀድሞ ፍቅር እንመልሰዋለን!››በማለት ተሳለቁ፡፡ የአቡነ ማቲያስ ወደ ቫቲካን መሄድ ለበርካታ ኢትዮጵያውያውያን እንግዳ ነገር ሆኖዋል፡፡ይህ ጉዳይ እንቆቅልሽ የሆነበት ካለ፤‹‹የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ›› የሚለውን መፅሐፍ ሲያነብ እንቆቅልሹ ይፈታለታል ባይ ነኝ፡፡.
                   አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

❖ሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን

ሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን

ምሥጢር ማለት ቃሉ የግሪክ ቋንቋ ሆኖ ቃሉ ከግዕዝና ከአማርኛ በቀጥታ የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም ድብቅ ፣ ስውር፣ ሽሽግ፣ ረቂቅ ፣ ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በቀር የማይገለጥ ማለት ነው፡፡ ለሁለት የሚከፈል ሲሆን ይኸውም የፍጡርሚሥጢርና የፈጣሪ ሚስጥር በመባል ይታወቃል፡፡ የፍጡር ምስጢር ሁለት ይዘት አለው፡፡ የሰውና የመላዕክት ምስጢር ይባላል፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው የፈጣሪ የእግዚአብሔር ሚስጥር ይህ የከበረ የተወደደ የሚናፈቅ የበረከት ስጦታ ነው፡፡ ብርሃነ አለም ሀዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል በከበረ ቃሉ ገልፆታል፡፡ “እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ /በክርስቶስ/ አምናችሁ የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱን የነብሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ በማይናገርና ክብር በሞላበት ሀሴት ደስ ይበላችሁ”፡፡ በማለት ስውር ረቂቅ ከሆነው ጸጋ እግዚአብሔር የምንሰጠው ሀብት መሆኑን በማብራራት ገልፆታል፡፡ በዚህ መሰረት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ከሚፈጸሙት ሚስጥራት በቁጥር 7 ተወስነው ተቀምጠዋል፡፡ ውሳኔነታቸው ለሰባቱ ሰማያት ስብዐተ እግዚአብሔር ለማይከፈልባቸው ከተሞች ገላጭ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰባት ሚስጥራት ቤተክርስቲያን የሚስጥርነታቸው ምክንያት በአይናችን ልናያቸው በእጃችን ልንዳስሳቸው የማንችል ልዩ ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በእነዚህ ሚስጥራት አማካኝነት የሚሰጡን ስለሆነ ነው፡፡ አበው ሲናገሩ በንባብ የተሰወረ ብሂል ምስጢር ይባላል ብለው ስውርነቱን ረቂቅነቱን ይናገራሉ፡፡ ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን የሚባሉት እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ፡፡
ጥምቀት
ሜሮን
ቁርባን
ክህነት
ንስሀ
ቀንዲል
ተክሊል ናቸው፡፡
1. ሚስጢረ ጥምቀት
ይህ ምሥጢረ ጥምቀት ከኃጢያት ነፃ የምንሆንበት ከዲያቢሎስ አገዛዝ አርነት የምንወጣበት ከእግዚአብሔር በጸጋ የምንወለድበት የምስጢር አይነት ነው፡፡ በቅሰዱሳት መጻህፍት እንደተገለጸው በነብየ እግዚአብሔር በቅዱስ ሕዝቅሌል ት.ሕዝ 36፡25 “ጥሩ ውሀንም ጥምቀትን እረጫችኋለሁ፡ እናንትም ትጠራላችሁ ከርኩስነታችሁም ሁሉ ከጣኦቶቻችሁ ሁሉ አጠራችኋለሁ አዲስ ልብ እሰጣችኋለው” በማለት የዚህን ምስጢር ክብርነት በረከትነት አምልቶ አስፍቶ ተናገሯል፡፡ በዚህ ሀሳብ ሌሎች ንፁሐን አበው ሀዋርያት ተባብረውታል፡፡ በምልአት ሰብከውታል፡፡ የሐዋ.2፡38 ፣ 1ቆሮ 6፡11 ፣ ዮሐ. 3፡5 ፣ ኤፌ 5፡26 ፣ ገላ 3፡27 ፣ ቲቶ 3፡5 ጥምቀት ዳግመኛ ተወልደን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምንገባበት ምስጢር ነው፡፡ ከመጸሕፍ ቅዱስ ውስጥ ጥምቀት ብዙ ምሳሌዎች ይኖሩታል፡፡ እነሆ ከማየአይኅ የዳነበትን መርከብ ቅዱስ ጴጥሮስ የጥምቀት ምሳሌ እንደሆነ ገልጾታል፡፡ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ምዕመናን ከሐጢያት ከጥፋት የሚድኑት በጥምቀት ነውና
ቅዱስ ጳውሎስም እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቀንበር ተላቀው የኤርትራን ባህር ተሻግረው ወደምድረ ርስት ያደረጉትን ጉዞ የጥምቀትን ምሳሌ አድርጎ አመስጥሮታል፡፡ 1ኛ ቆሮ 10፡1-2 ምዕመናን ባህረ ኃጢያትን ተሻግረው ምድረ ርስተ መንግስተ ሰማያትን የሚወርሱት በጥምቀት ነውና፡፡ ዳግመኛም ይህ ብርሃናዊ ሐዋርያ ጥምቀትን በሞትና በመቃብር ይመስለዋል፡፡ ሮሜ 6፡3-4 ቆላ 2፡12 በሞት ጊዜ ነፍስና ስጋ እንደሚለያዩ በጥምቀትም አሮጌው ሰውነት ይሞታል ይቀበራል አዲስ ሰውነት አዲስ ሕልውናን ይጀምራልና፡፡
2. ምስጢረ ሜሮን
ይህ ቃል የጽርዕ ቋንቋ ነው ትርጉሙም መአዛ ያለው የሚያውድ ፣ የሚጣፍጥ፣ ልብ የሚመስጥ ፣ ጣዕም ያለው መልኩ ጽርየቱ ዘይት ነው፡፡ በግዕዝ ቅብዕ፣ ቅብዐ ሜሮን ይባላል፡፡ ከብዙ እጽዋት ተቀምሞ የሚሰራ ነው፡፡ ሕዝበ እስራኤልን የሚያስተዳድሩ የእግዚያብሔር እንደራሴዎች ነገስታትን መሲሀን የሚባሉት ለዚህ ቅብ ተቀብተው ስለሚነግሱ ነው፡፡ ዘፍ 20፡23 1ኛ ሳሙ 10፡1 ዘዳ 28፡41 1ኛ ሳሙ 9፡6 1ኛ ነገስት 1፡34 ይህ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሚገለገልባቸው የቤተመቅደስ ነዋያተ ቅድሳትን አስቀድሞ በዚህ መታተም አለባቸው፡፡ ከተቀቡ በኋላ ለቤተ መቅደስ እንጂ ለተራ አገልግሎት አይውሉም ስለ ቅብዐ ሜሮን ቅዱስ መጽሐፍን የፃፉ ሰዎች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ቅብዐት ይሉታል፡፡ 2ኛ ቆሮ 1፡21 ዮሐ 2፡20 ቅብዕን በመንፈስ ቅዱስ ማህተምን ይሉታል፡፡ ኤፊ 1፡13 ፣4፡30 ይህ ቅብዓ ማህተመ ሕይወት በመሆኑ ለአገልግሎት ይውላል፡፡
3. ምሥጢረ ቁረባን
ይህ ቃል የሱርስት ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም አምኃ ስጦታ ማለት ነው፡፡ ሥጋውና ደሙ የተሰጠን በነፃ ያለ ዋጋ ሳይገባን በችሮታ ነውና፡፡ በቤተክርስቲያን ምሥጢራት ሁሉ መደምደሚ ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ መስዋዕት ማቅረብ የተጀመረው በአዳም ጊዜ ሲሆን ከአዳም እስከ ሙሴ የተነሱ አበው ሁሉ በህገ ልቦና ለእግዚአብሔር መስዋት ይሰው ቁርባን ያቀርቡ ነበር፡፡ መስዋዕታቸው ከእንሰሳ ቁርባናቸው ከእህልና ከአትክልት ማለት ከስንዴ እህል፣ ከወይን ፍሬ የሚቀርብ ነው፡፡ ዘመነ ኦሪት በብሉይ ኪዳን በሙክራብ የተሰዋ እንሰሳት ሁሉ በአዲስ ኪዳን በቤተክርስቲያን ለሚሰዋው ሁሉ የክርስቶስ ሥጋና ደም ምሳሌ ነበር፡፡ መልከ ጼዴቅ ያበረከተው ኅብስተ አኮቴት ጽዋዐ በረከት ለአምላክ የሥጋውና የደሙ ምሳ ሆነው አልፈዋል፡፡ ከምሥጢራት አንዱ መሆኑ ሕብስቱ ተለውጦ የክርስቶስ ሥጋ ጽዋው ተለውጦ የክርስቶስ ደም ሲሆን አይታይም፡፡ ነገር ግን እምነት ያለው ሁሉ በእምነት መነጽር ይመለከተዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ሳይታይ የሚወደድን ሕይወት ለማግኘት ከቁርባን በፊት ንስሐ መግባት ለአስራ ስምንት ሰዓት መጾም አለበት፡፡ ንጽሕናውን በጠበቅ አለበት፡፡ መምክረ ካህን ጸንቶ መገኘት ያስፈልጋል፡፡
4. ምሥጢረ ክህነት
ይህ ቋንቋ የግዕዝ ቋንቋ ነው፡፡ ተክህነ አገልገለ ከሚለው ግስ የወጣ ነው፡፡ ክህነት የተጀመረው በአባታች አዳም ነው፡፡ ክህነት የአገልግሎት ስም ሆኖ የቤተክርስቲያን ከፍተኛ መንፈሳዊ ማዕረግ ነው፡፡ እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ በልጅነት አክብሮ ነብይና ካህን አድርጎ ሾሞ በኦሪት በወንጌል ሥርዓት እስኪወሰን ድረስ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ የነበሩ አበው በበረከት አበው ከእግዚአብሔር እየተሾሙ ትንቢትን ክህነት ከቅዱሱ መንፈስ እየተቀበሉ (እየተሾሙ) በነብይነታቸው ያለውን የሚመጣውን ሲገልጽ ሲያስተምሩ በሀብተ ክህነታቸው መስዋዕት ሲቀርቡ ነበር፡፡ ክህነት በዘመነ ኦሪት ለሌዊ ነገድ ከተሰጠ በኋላ ሲወርድ ሲወራረድ እስከ ክርስቶስ ደርሷል፡፡ ታላቁ ሊቀ ካህናት እየሱስ ክርስቶስ እንደ ብሉይ ኪዳን መስዋዕት እንሰሳ ሳሆን እራሱን መስዋዕት፣ እርሱ ሰዋዒ ሆኖ ወደ መቅደስ ገብቷል፡፡ ዮሐ 20፡22 ማሬ 18፡18 1ኘና ቆሮ 4፡1 ማሬ 28፡20
5. ምሥጢረ ንስሐ
ይህ ቃል የግዕዝ ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም በሰሩት ኃጢያት መጸጸት ምነው ባልሰራሁት ባላደረኩት ብሎ ማልቀስ ወደ ኃጢያት ላለመመለስ መወሰን፣ በሕጉ ጸንቶ ለመኖር ቃል መግባት፡፡ ክርስቲያን በጥምቀት ከአለም ክፉ ስራዎች ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ህይወቱ ለክርስቶስ የተሰጠ ነው፡፡ ሮሜ 12፡1 የመጨረሻው ግቡና ዓላማው ሥርየተ ኃጢያትን ማግኘት እና የዘላለም ሕይወት መወረስ ነው፡፡ አካሉ የመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ 1ቆሮ 6-19
6. ምሥጢረ ቀንዲል
ይህ ቃል የላቲን ቋንቋ ነው ትርጉሙም ፍፁም መብራት ማለት ነው፡፡ ከሰባቱ ሚስራት አንዱ ቀንዲል ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘይት የፈውስ ምልክት ነው፡፡ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሰቃዩ ህሙማን ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ቁስለኞች እየተቀቡ ይፈወሱ ነበር፡፡ ኢሳ 1፡6 ሉቃ 10፡34 ራዕ 3፡18 ማር 6፡13 ይህ ቅብዓተ በሐዲስ ኪዳን ለሚጠመቁ ከሚደረግ ቅብዐ ሜሮን ጋር ግንኙነት የለውም ራሱን የቻለ ሕሙማነ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ሕሙማነ ነፍስ ኃጥአን የሚቀቡት ፈውስ የሚያገኙበት ነው፡፡ ማር 6፡13 ያዕ 5፡13-15 ራዕ 1፡17፡፡
7. ምሥጢረ ተክሊል
ይህ ማለት “ተከለለ” ተቀናጀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ በሥርዓተ ጋብቻ ቅደም ተከተል መሰረት በመተጫጨት እና በቃል ኪዳን የተመሰረተ ጋብቻ በተክሊል ይፈጸማል፡፡ ቤተክርስቲያን ምስክርነት የሚፈጸመው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በተክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በትክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ዘፍ 1፡27-28 ፣ 2-18 ማቴ 19-4 እነዚህን ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አውቀን ተረድተን የእምነታችን ፍጻሜ የሆነውን አምላካችንን ለተፈጠርንለት ዓላማ በመገዛት የነፍሳችንን መዳን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡
ለዚህም ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር እንዲረዳን የወላዲተ አማላክ አማላጅነት እንዳይለየን የጻድቃን ፀሎት የቅዱሳን በረከት እንዳይለየን ፈቃዱ ይሁንልን አሜን!!!

ጥምቀት
ሜሮን
ቁርባን
ክህነት
ንስሀ
ቀንዲል
ተክሊል ናቸው፡፡
1. ሚስጢረ ጥምቀት
ይህ ምሥጢረ ጥምቀት ከኃጢያት ነፃ የምንሆንበት ከዲያቢሎስ አገዛዝ አርነት የምንወጣበት ከእግዚአብሔር በጸጋ የምንወለድበት የምስጢር አይነት ነው፡፡ በቅሰዱሳት መጻህፍት እንደተገለጸው በነብየ እግዚአብሔር በቅዱስ ሕዝቅሌል ት.ሕዝ 36፡25 “ጥሩ ውሀንም ጥምቀትን እረጫችኋለሁ፡ እናንትም ትጠራላችሁ ከርኩስነታችሁም ሁሉ ከጣኦቶቻችሁ ሁሉ አጠራችኋለሁ አዲስ ልብ እሰጣችኋለው” በማለት የዚህን ምስጢር ክብርነት በረከትነት አምልቶ አስፍቶ ተናገሯል፡፡ በዚህ ሀሳብ ሌሎች ንፁሐን አበው ሀዋርያት ተባብረውታል፡፡ በምልአት ሰብከውታል፡፡ የሐዋ.2፡38 ፣ 1ቆሮ 6፡11 ፣ ዮሐ. 3፡5 ፣ ኤፌ 5፡26 ፣ ገላ 3፡27 ፣ ቲቶ 3፡5 ጥምቀት ዳግመኛ ተወልደን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምንገባበት ምስጢር ነው፡፡ ከመጸሕፍ ቅዱስ ውስጥ ጥምቀት ብዙ ምሳሌዎች ይኖሩታል፡፡ እነሆ ከማየአይኅ የዳነበትን መርከብ ቅዱስ ጴጥሮስ የጥምቀት ምሳሌ እንደሆነ ገልጾታል፡፡ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ምዕመናን ከሐጢያት ከጥፋት የሚድኑት በጥምቀት ነውና
ቅዱስ ጳውሎስም እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቀንበር ተላቀው የኤርትራን ባህር ተሻግረው ወደምድረ ርስት ያደረጉትን ጉዞ የጥምቀትን ምሳሌ አድርጎ አመስጥሮታል፡፡ 1ኛ ቆሮ 10፡1-2 ምዕመናን ባህረ ኃጢያትን ተሻግረው ምድረ ርስተ መንግስተ ሰማያትን የሚወርሱት በጥምቀት ነውና፡፡ ዳግመኛም ይህ ብርሃናዊ ሐዋርያ ጥምቀትን በሞትና በመቃብር ይመስለዋል፡፡ ሮሜ 6፡3-4 ቆላ 2፡12 በሞት ጊዜ ነፍስና ስጋ እንደሚለያዩ በጥምቀትም አሮጌው ሰውነት ይሞታል ይቀበራል አዲስ ሰውነት አዲስ ሕልውናን ይጀምራልና፡፡
2. ምስጢረ ሜሮን
ይህ ቃል የጽርዕ ቋንቋ ነው ትርጉሙም መአዛ ያለው የሚያውድ ፣ የሚጣፍጥ፣ ልብ የሚመስጥ ፣ ጣዕም ያለው መልኩ ጽርየቱ ዘይት ነው፡፡ በግዕዝ ቅብዕ፣ ቅብዐ ሜሮን ይባላል፡፡ ከብዙ እጽዋት ተቀምሞ የሚሰራ ነው፡፡ ሕዝበ እስራኤልን የሚያስተዳድሩ የእግዚያብሔር እንደራሴዎች ነገስታትን መሲሀን የሚባሉት ለዚህ ቅብ ተቀብተው ስለሚነግሱ ነው፡፡ ዘፍ 20፡23 1ኛ ሳሙ 10፡1 ዘዳ 28፡41 1ኛ ሳሙ 9፡6 1ኛ ነገስት 1፡34 ይህ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሚገለገልባቸው የቤተመቅደስ ነዋያተ ቅድሳትን አስቀድሞ በዚህ መታተም አለባቸው፡፡ ከተቀቡ በኋላ ለቤተ መቅደስ እንጂ ለተራ አገልግሎት አይውሉም ስለ ቅብዐ ሜሮን ቅዱስ መጽሐፍን የፃፉ ሰዎች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ቅብዐት ይሉታል፡፡ 2ኛ ቆሮ 1፡21 ዮሐ 2፡20 ቅብዕን በመንፈስ ቅዱስ ማህተምን ይሉታል፡፡ ኤፊ 1፡13 ፣4፡30 ይህ ቅብዓ ማህተመ ሕይወት በመሆኑ ለአገልግሎት ይውላል፡፡
3. ምሥጢረ ቁረባን
ይህ ቃል የሱርስት ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም አምኃ ስጦታ ማለት ነው፡፡ ሥጋውና ደሙ የተሰጠን በነፃ ያለ ዋጋ ሳይገባን በችሮታ ነውና፡፡ በቤተክርስቲያን ምሥጢራት ሁሉ መደምደሚ ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ መስዋዕት ማቅረብ የተጀመረው በአዳም ጊዜ ሲሆን ከአዳም እስከ ሙሴ የተነሱ አበው ሁሉ በህገ ልቦና ለእግዚአብሔር መስዋት ይሰው ቁርባን ያቀርቡ ነበር፡፡ መስዋዕታቸው ከእንሰሳ ቁርባናቸው ከእህልና ከአትክልት ማለት ከስንዴ እህል፣ ከወይን ፍሬ የሚቀርብ ነው፡፡ ዘመነ ኦሪት በብሉይ ኪዳን በሙክራብ የተሰዋ እንሰሳት ሁሉ በአዲስ ኪዳን በቤተክርስቲያን ለሚሰዋው ሁሉ የክርስቶስ ሥጋና ደም ምሳሌ ነበር፡፡ መልከ ጼዴቅ ያበረከተው ኅብስተ አኮቴት ጽዋዐ በረከት ለአምላክ የሥጋውና የደሙ ምሳ ሆነው አልፈዋል፡፡ ከምሥጢራት አንዱ መሆኑ ሕብስቱ ተለውጦ የክርስቶስ ሥጋ ጽዋው ተለውጦ የክርስቶስ ደም ሲሆን አይታይም፡፡ ነገር ግን እምነት ያለው ሁሉ በእምነት መነጽር ይመለከተዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ሳይታይ የሚወደድን ሕይወት ለማግኘት ከቁርባን በፊት ንስሐ መግባት ለአስራ ስምንት ሰዓት መጾም አለበት፡፡ ንጽሕናውን በጠበቅ አለበት፡፡ መምክረ ካህን ጸንቶ መገኘት ያስፈልጋል፡፡
4. ምሥጢረ ክህነት
ይህ ቋንቋ የግዕዝ ቋንቋ ነው፡፡ ተክህነ አገልገለ ከሚለው ግስ የወጣ ነው፡፡ ክህነት የተጀመረው በአባታች አዳም ነው፡፡ ክህነት የአገልግሎት ስም ሆኖ የቤተክርስቲያን ከፍተኛ መንፈሳዊ ማዕረግ ነው፡፡ እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ በልጅነት አክብሮ ነብይና ካህን አድርጎ ሾሞ በኦሪት በወንጌል ሥርዓት እስኪወሰን ድረስ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ የነበሩ አበው በበረከት አበው ከእግዚአብሔር እየተሾሙ ትንቢትን ክህነት ከቅዱሱ መንፈስ እየተቀበሉ (እየተሾሙ) በነብይነታቸው ያለውን የሚመጣውን ሲገልጽ ሲያስተምሩ በሀብተ ክህነታቸው መስዋዕት ሲቀርቡ ነበር፡፡ ክህነት በዘመነ ኦሪት ለሌዊ ነገድ ከተሰጠ በኋላ ሲወርድ ሲወራረድ እስከ ክርስቶስ ደርሷል፡፡ ታላቁ ሊቀ ካህናት እየሱስ ክርስቶስ እንደ ብሉይ ኪዳን መስዋዕት እንሰሳ ሳሆን እራሱን መስዋዕት፣ እርሱ ሰዋዒ ሆኖ ወደ መቅደስ ገብቷል፡፡ ዮሐ 20፡22 ማሬ 18፡18 1ኘና ቆሮ 4፡1 ማሬ 28፡20
5. ምሥጢረ ንስሐ
ይህ ቃል የግዕዝ ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም በሰሩት ኃጢያት መጸጸት ምነው ባልሰራሁት ባላደረኩት ብሎ ማልቀስ ወደ ኃጢያት ላለመመለስ መወሰን፣ በሕጉ ጸንቶ ለመኖር ቃል መግባት፡፡ ክርስቲያን በጥምቀት ከአለም ክፉ ስራዎች ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ህይወቱ ለክርስቶስ የተሰጠ ነው፡፡ ሮሜ 12፡1 የመጨረሻው ግቡና ዓላማው ሥርየተ ኃጢያትን ማግኘት እና የዘላለም ሕይወት መወረስ ነው፡፡ አካሉ የመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ 1ቆሮ 6-19
6. ምሥጢረ ቀንዲል
ይህ ቃል የላቲን ቋንቋ ነው ትርጉሙም ፍፁም መብራት ማለት ነው፡፡ ከሰባቱ ሚስራት አንዱ ቀንዲል ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘይት የፈውስ ምልክት ነው፡፡ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሰቃዩ ህሙማን ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ቁስለኞች እየተቀቡ ይፈወሱ ነበር፡፡ ኢሳ 1፡6 ሉቃ 10፡34 ራዕ 3፡18 ማር 6፡13 ይህ ቅብዓተ በሐዲስ ኪዳን ለሚጠመቁ ከሚደረግ ቅብዐ ሜሮን ጋር ግንኙነት የለውም ራሱን የቻለ ሕሙማነ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ሕሙማነ ነፍስ ኃጥአን የሚቀቡት ፈውስ የሚያገኙበት ነው፡፡ ማር 6፡13 ያዕ 5፡13-15 ራዕ 1፡17፡፡
7. ምሥጢረ ተክሊል
ይህ ማለት “ተከለለ” ተቀናጀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ በሥርዓተ ጋብቻ ቅደም ተከተል መሰረት በመተጫጨት እና በቃል ኪዳን የተመሰረተ ጋብቻ በተክሊል ይፈጸማል፡፡ ቤተክርስቲያን ምስክርነት የሚፈጸመው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በተክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በትክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ዘፍ 1፡27-28 ፣ 2-18 ማቴ 19-4 እነዚህን ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አውቀን ተረድተን የእምነታችን ፍጻሜ የሆነውን አምላካችንን ለተፈጠርንለት ዓላማ በመገዛት የነፍሳችንን መዳን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡
ለዚህም ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር እንዲረዳን የወላዲተ አማላክ አማላጅነት እንዳይለየን የጻድቃን ፀሎት የቅዱሳን በረከት እንዳይለየን ፈቃዱ ይሁንልን አሜን!!!

Saturday, March 26, 2016

❖የመናፍስት ውጊያ

የመናፍስት ውጊያ፥

       ክፉ መንፈስ ሰዎችን በተለያየ ምክንያት ሊይዛቸው ይችላል። ለምሳሌም ከቤተሰብ በሚወረስ የባዕድ (የጣዖት) አምልኮ፣ የኃጢአት ሕይወትን በመምራት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ባልተመሠረተና ባልጸና ክርስትና በመመላለስ፣ ለአጋንንት የተዘጋጁ መስዋዕቶችን በመካፈል (1ቆሮ. 10፣19-21)፣ … ሊሆን ይችላል። አጋንንትን ከሰው ውስጥ የማሰወጣት ሥልጣን በክርስቶስ ኢየሱስ ላመኑ ሁሉ የተሰጠ ስልጣን ነው (ማር. 16፣17)። እግዚአብሔር ያጎናጸፈን ክብር አጋንንትን ከማስወጣት የበለጠ ነው። እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ (ሉቃ. 10፣19-20)። ሰይጣን እንግዳ የሆነ ጠላት ስለ ሆነ የእግዚአብሔር መቅደስ (ማደሪያ) በሆነው ሰው ውስጥ መኖር አይፈቀድለትምና ታዝዞ መውጣት አለበት። ሰይጣን ከሰው ሊወጣ የሚችለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብቻ መሆኑን ግን አበክረን ለመግለጽ እንወዳለን። ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት (ሉቃ. 10፣17፤ ፊል. 2፣9-10) ጳውሎስ ግን ዘወር ብሎ መንፈሱን፦ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ (የሐዋ. 16፣18)።
ደግሞም ሰይጣን የተሸነፈ ባላጋራ መሆኑን፣ በእኛ ላይ ምንም ዓይነት ሥልጣን እንደሌለውና ዕድል ፈንታው ታዝዞ ወደ ዘላለም መኖሪያው ወደ ሲኦል መግባት እንደሆነ ልናውቅ ይገባል (ሉቃ. 10፣18፤ ራእ. 12፣10-11)። በእርግጥ አንዳንዱ የአጋንንት እስራት ብርቱ ጾምና ጸሎት ሊያስፈልገው ቢችልም አጋንንት በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ሲታዘዙ ፈርተውናና ተንቀጥቅጠው ካልወጡና ከዚህ አልፈው ስለሚወጡበት ቀን ከተደራደሩ ያ የፈውስ አሰራር ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ ማረጋገጥ ይቻላል። እስኪ እናስተውል የተሸነፈና የወደቀ ጠላት እንዴት ብሎ ዛሬ አልወጣም በመረጥኩት ቀን እንጂ ማለት ይችላል? ይህ በሚሆን ጊዜ እፈውሳለሁ የሚለውን ሰው ማንነት በሚገባ መመርመር ይገባል። ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚታለሉት እንፈውሳለን የሚሉት ሰዎች በሚጠቀሙት ሰይጣንን የማናዘዝ ክፉ ጥበብ በመወናበድ ነው። ሰይጣን እኮ ምንም እውነት የሌለው ጠላት ነው። ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና (ዮሐ. 8፣44)። ሰይጣን የተናገረውን ውሸት በመስማትና በማመን ስንት ቤተሰብ፣ ትዳር፣ ጓደኝነት፣ … ፈርሶአል። በቅርቡ አንዲት እህት ስናነጋግር በውስጧ ያደረው ጋኔን ሲለፈልፍ ድግምት ያደረገችብሽ ወላጅ እናትሽ ናት ብሎአት ከእናቷ ጋር መለያየቷን ነግራናለች። ሰይጣን ከሰው ከወጣ በኋላ ተመልሶ የሚገባበትን ምክንያት በተመለከተ፦ ዋናው ምክንያት ያ የተፈወሰው ሰው በእግዚአብሔር ቃል በመኖር ሕይወቱን መጠበቅ ሳይችል ሲቀር፣ በቀድሞ ሕይወቱ ከነበረው ልምምድ ያልተቆረጠ ነገር ሲኖረው … (ሉቃ. 11፣24-26፤ ዮሐ. 5፣14) ሊሆን ይችላል እንጂ ድግምቱ ታድሶበት፣ ከተፈወሰ በኋላ በመጣበት መንገድ ተመልሶ ስለ ሄደ፣ … የሚለው ሃሳብ ትክክል አይደለም። ደግሞም ሰዎችን ሳይፈወሱ በየጸበሉ ዘመናት እንዲቆጥሩ ማድረግ የሰይጣን ጥበብ ነው። በመጀመሪያ በመጎሳቆል ብዛት ጤናቸው ሊታወክና በበሸታ ሊሞቱ ይችላሉ። እንዲሁም መማር፣ መሥራት፣ ማግባት … የሚችሉበትን መልካም ጊዜ ያባክንና ጓደኞቻቸው በሕይወት አልፈዋቸው እንደሄዱ በማሳየት በተስፋ መቁረጥ ወደ ጥፋት ሁኔታ ሊመራቸው፣ ራሳቸውንም እንዲያጠፉ ሊያደርግም ይችላል። የዓምድ ጥበት ስለሚወስነን እንጂ ብዙ ነገር ለመግለጽ እንወድ ነበር። ለማጠቃለልም በመጀመሪያው ጥያቄሽ ላይ ያነሳሻቸው ሃሳቦች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆናቸውን አረጋግጠን ለመናገር እንወዳለሁ።
አንዳንድ ጊዜ ሴቶች ሱሪ አድርገው፣ ጥፍር ቀለም ተቀብተው፣ ፀጉራቸውን በዊግ (ሰው ሠራሽ ፀጉር) ተሠርተው፣ … ሲመጡ ርኩስ መንፈስ ያለባቸው ሰዎች እንዲህ ሆነሽ አትገቢም ብለው በድንጋይ ጭምር ሲደበድቡ አይቼአለሁ። አልፎ አልፎም በርኩስ መንፈስ የተያዙትም ሰዎች የሚገላግሉ መስለው ተመቺዋን ብቻ እጆቿን በመያዝ የሚያስደበድቡም አሉ። እኔ መጠየቅና ለምን? ማለት ስለሚቀናኝ፣ ሰይጣንን በእግዚአብሔር ቤት ሥርዓት አስከባሪ ያደረገው ማን ነው? ብዬ ስጠይቅ እመቤቴ፣ ሚካኤል፣ …መንፈሱን አዝዘውት ነው ይሉኛል። ይህስ በእግዚአብሔር ቃል እንዴት ይታያል? ሰይጣንስ ከቅዱሳን ጋር ምን ሕብረት አለው?
ይህ አሠራር ፈጽሞ ስሕተት ነው፤ ሰይጣን በምንም ዓይነት ሁኔታ የእግዚአብሔር ቤት ሥርዓት አስከባሪና ሕግ አስጠባቂ ለመሆን አይችልም። … ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? (2ቆሮ. 6÷14-15)። ብዙዎቻችን ስለ ሰይጣን ባሕርይና ስለ እግዚአብሔር የፈውስ አሰራር መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ስለሌለን እንሳሳታለን። በተለይም በዘመኑ ያለው የፈውስ አሠራር የእግዚአብሔርን ክብር ከመግለጽ ይልቅ በአብዛኛው ሰይጣንን በማናዘዝ (ቃለ መጠይቅ በማድረግ)፣ እርሱን በማዳመጥና ሐሳቡን እንደ ትክክለኛ መልዕክት በማስተላለፍ ላይ ያተኮረ ነው። ይህ ዓይነቱ አካሄድ ሰይጣናዊና አጥማቂ ነን የሚሉትን ሰዎች ዝና በመገንባት ላይ የተመሠረተና እንዲሁም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የስህተት ትምህርት በማስተላለፍ ሰዎችን ለበለጠ እስራት እየዳረገ ያለ ነው። መጽሐፍ ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና። እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል (2ቆሮ. 11፣14-15) ይላልና ሰይጣን በሚናገረው ውስጥ ምንም ዓይነት መልካም ነገር እንደሌለ መረዳት ይገባናል፡ ሴቶች እንዲህ ሆነው አይገቡም፣ በዛሬው ዕለት አይሰገድም እያለ ሰላማዊ የሆነውን የቤተ ክርስቲያን የአምልኮ ሥርዓት (ቃለ እግዚአብሔር መስማትን፣ ጸሎትና ምህላን፣ ስግደትን፣ …) ሲረብሽ ታዞ ነው ተዉት ማለት የሰይጣን ተከታይ ከመሆን የተለየ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም። አንዲት እህት ለጸበል በሄደችበት ቦታ ልትጠመቅ ስትል ሰይጣን በአንዲት ሴት ውስጥ ተገልጾ ንስሐዋን አልጨረሰችምና ቀድማ ንስሐ ትግባ አለበለዚያ አትጠመቅም አለኝ። ኧረ እንዴት ይሆናል! እርሱ ከአምላኬ ጋር ያለኝን የንስሐ ጉዳይ የት ያውቅና ነው? ብል ሲገደድ እውነት ይናገራልና ንስሐ ካልገባሽ አትጠመቂም በማለት ሌሎች ተጠማቂዎች ለረብሻና ለድብድብ እንደተነሡባት መስክራለች።
ሰይጣን ዓላማው እኛን የነፍሳችን ድኅነት ብቸኛ መሠረት ከሆነው ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መለየት ነውና በመንፈሳዊ ልብ ማስተዋል አለብን። ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው። ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ … (2ቆሮ. 4፣3-6)። ለምሳሌም የቅዱሳን ስም ሲጠራበት ኧረ ተቃጠልኩ፣ ዕንባዋ አቃጠለኝ፣ … ስማቸውን አትጥሩብኝ ይላል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲሉት ግን ችግር የለብኝም ይላል። እንግዲህ ዓላማው የኃጢአት ዕዳችን ተከፍሎ ነጻ የወጣንበት፣ የገነት በር የተከፈተበት፣ ሰይጣን ለዘላለም የተሸነፈበት፣ ዓለምን ለማሳለፍ የሚመጣውን ፈራጅና የጌታን ስም አቃለን እንድንተው ለማድረግ መሆኑ ይግባን። ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታና አዳኝና እንደሆነ የማይሰበክበት አጋንንትም በስሙ የማይታዘዙበት አገልግሎት ከእግዚአብሔር አለመሆኑን ልብ ልንል ይገባል (ፊል. 2፣6-11)። ከዚህ በላይ ለጠቀስናቸው ስሕተቶች በተለይ የሚጋለጡት ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት የሌላቸው የእግዚአብሔር ጽድቅ የሆነውን ክርስቶስ ኢየሱስን ከማየት ይልቅ ምልክትና ድንቅ ፍለጋ የሚንከራተቱ ምስኪን ወገኖቻችን ናቸው።

Sunday, January 17, 2016

❖መልካም እድል

መልካም ዕድል

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ ሲመላለስ ራሱን የሚያስጠጋበት ጎጆ፣ የሚጸልይበት ልዩ ስፍራ አልነበረውም፡፡ በየጫካው ማደርና መጸለይ ልማዱ ነበር፡፡ ስለ እኛ ሲል የመረጠው ድህነት ልክ አልነበረውም፡፡ እኛ ከሰው ማነስ ያስጨንቀናለ፤ እርሱ ግን ከሰማይ አእዋፋት ከምድር ቀበሮች ያነሰ ኑሮ ኖሯል /ማቴ. 8፡20/፡፡  እርሱ ሞቱ ብቻ ሳይሆን ኑሮውም ቤዛችን ነበር፡፡ ስለ እኛ ድሃ ካልሆነ እኛ በመለኮት ብልጥግና መሞላት አንችልም፡፡ አብዛኛዎቹ የአደባባይ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ ነበሩ፡፡ በራቸውን ከፍተው የሚያስተናግዱት ግን ጥቂቶች ነበሩ፡፡ ከእነዚያ ጥቂቶች መካከል ማርታና ማርያም ተጠቃሾች ናቸው፡፡

      “ሲሄዱም እርሱ ወደ አንዲት መንደር ገባ፤ ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤትዋ ተቀበለችው” /ሉቃ. 10፡38/፡፡

 እርሱ በመንደራችን ያልፋል፣ ወደ ቤታችን የሚገባው ግን ስንከፍትለት ብቻ ነው፡፡ በመንደራችን ለማለፍ አያስፈቅድም፡፡ ወደ ቤታችን ለመግባት ግን ፈቃዳችንን ይጠይቃል፡፡ ወዳጅን የምንቀበለው በሌላ ቤት ሳይሆን በራሳችን ቤት ነው፡፡ መቀበል በርን መክፈት፣ ጓዳን ማሳየት፣ ማስተናገድ ነው፡፡ ፈሪሳዊው ስምዖን ጌታን እቤቱ ተቀብሎታል፡፡ ግን ቤቱ የተቀበለው ታዋቂ የሆነውን ጌታ በመጋበዝ ለዝነኛነት ነው፡፡ ስለዚህ በቤቱ ጋብዞ ምንም አላደረገለትም፡፡ ለአንድ ተራ እንግዳ የሚቀርበውን ነገር እንኳ አላደረገለትም፡፡ ያቺ ኃጢአተኛ ሴት ግን ያለ ቤቷ ጌታን አስተናገደችው፡፡ ቤቱ የስምዖን ነው፡፡ በዕንባዋና በሽቱዋ ግን እግሩን ያጠበችው ኃጢአተኛዋ ሴት ናት፡፡ ስምዖን ቤቱን ያቺ ሴት ራሷን አቀረበች፡፡ ስምዖን ጋብዞ ታዘበው ያቺ ሴት ግን ኃጢአቷን ተናዘዘችለት /ሉቃ. 7፡36-50/፡፡ እርሱ የሚከብረው በሳሎናችን ሳይሆን በልባችን ነው፡፡ ማርታ ለጌታ በሯም ልቧም ክፍት ነበረ፡፡ ከፍትፍቱ ፊቱ እንዲሉ ፍትፍቱም ፊቱም ሁሉም አልቀረባትም፡፡

ይህች ማርታ፡- “ማርያም የምትባል እህት ነበረቻት፣ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች” /ሉቃ. 10፡39/፡፡ ማርያም ምንም እንኳ ጌታ ትልቅ እንግዳዋ ቢሆንም ለጌታ ከመስጠቷ በፊት ከእርሱ መቀበልን ፈልጋለች፡፡ ከምትሰጠው የሚሰጣት በልጦባት እግሩ ሥር ተቀምጣ ነበር፡፡ ለጌታ አደባባዩም ሆነ ቤቱ ሁሉም ለእርሱ ቃሉን ማወጂያ ነው፡፡ አገልግሎቱ ባለበት ቦታና ጊዜ ሁሉ ይቀጥል ነበር እንጂ በጊዜና በቦታ የተገደበ አልነበረም፡፡ ማርያም የቃሉን መጽናናት ትፈልግ ነበር፡፡ ያለ ቃሉ ሕይወት እንደሌላት ታውቅ ነበር፡፡ ትላንትን ለመርሳት ዛሬን ለመጋፈጥ፣ ነገን ለመናፈቅ ቃሉን ትሻ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የትላንት ካሣ፣ የዛሬ አቅም፣ የነገ ተስፋ ነው፡፡

“ማርታ ግን አገልግሎት ስለበዛባት ባከነች፤ ቀርባም፡- ጌታ ሆይ፣ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አያገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት” አለችው፡፡ማርታ ለጌታና ለደቀ መዛሙርቱ ማዕድ ለማቅረብ ከፍ ዝቅ ትል ነበር፡፡ ቃሉ ግን አልተቻትም፡፡ አገልግሎት እንደ ነበር ይናገራል፡፡ አገልግሎት አገልጋዮችን መደገፍም ነው፡፡ ለሚያስተምሩት ማዕድ ማሰናዳትም አገልግሎት ነው፡፡ አገልግሎት መስበክ፣ መዘመር ብቻ አይደለም፡፡ የማይታይ ደጀን መሆንም አገልግሎት ነው፡፡ ማርታ ግን ብቻዋን ባከነች፡፡ በየዓይነቱ ምግቡን ለማቅረብ ስትጣደፍ ጊዜውና አቅሟ አልበቃ አላት፡፡ ማርያም ግን በቤቷ እንግዳ ሆና ታየቻት፤ ስለዚህ ማርያምን ጌታ ጋ ከሰሰቻት፡፡ በብዙ አገልግሎት መድከም መልካም ቢሆንም ካልተጠነቀቁ ግን ከሳሽ ያደርጋል፡፡ የሌሎችን አለማገልገል ያሳያል፡፡ ይህንን ሐሜትም ለጌታ እንድንናገር ያደርጋል፡፡ ማገልገል የሌሎችን አለማገልገል ካሳየ ፍቅር አልባ ያደርጋል፡፡ ጌታንም፡- “አይገድህምን?” አለችው፡፡ ኤልያስ ብቻዬን ቀረሁ እንዳለ ጉዳዩ ወደ ጌታ መጣ፡፡ አገልግሎት ውጤታማ የሚሆነው ሲጠባበቁ አይደለም፡፡ የቻሉትን በጸጋ ድጋፍ ተወጥቶ ማለፍ ነው፡፡ ፉክክርና መጠባበቅ ካለ አገልግሎት አይጓዝም፡፡ እግዚአብሔር በአንድ ሙሴ አንድ ሚሊየን ሕዝብን ነጻ አውጥቷል፡፡ አንድ የቆረጠ እልፍ ሥራ ይሠራል፡፡



ጌታ ለማርታ አዘነላት፡፡ ማርታ ይህን ቃል ስትናገር ጉባዔው ተፈቷል፡፡ የሚማሩት ትምህርቱ ተቋርጦባቸዋል፡፡ ስንካሰስ ጉባዔ ይፈታል፡፡ ምእመናን ይጎዳሉ፡፡ ምግብ ለማቅረብ ጠርተናቸው ነገር ተመጋቢ ሆነው ይታመማሉ፡፡ አዎ የማዕድ አገልግሎት የቃሉን አገልግሎት እንዳያደናቅፍ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሐዋርያት ሰባት ዲያቆናትን የሾሙበት ምሥጢር ይህ ነው /የሐዋ. 6፡2/፡፡ ዛሬም በአሠራር ተይዘን ለማገልገል ጊዜ እንዳናጣ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

ጌታ ማርታን፡- “ማርታ፣ ማርታ በብዙ ትጨነቂአለሽ ትታወኪማለሽ፣ የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም” /ሉቃ.10፤41-42/

 ማርታ ጭንቀቷ ለምሳ ብቻ አይደለም፡፡ ጭንቀቷ ለዓመት ቀለብ ይመስላል፡፡ ጉዳዩ ትንሽ ጭንቀቷ ግን ትልቅ ነበር፡፡ በርግጥም የሚያስፈልገው ምን ያህል ነው? አሁን የሚያስፈልገውስ ምንድነው? የሚያስፈልገን ብዙ ወዳጅ ብዙ ንብረት አይደለም፡፡ ጥቂት ነገር ነው፡፡ ሕይወትን በዕለት ብንኖር የሚያስፈልገው ጥቂት ነው፡፡ መጨነቅ፣ መታወክ፣ መበጥበጥ፣ መተራመስ፣ እንቅልፍ ማጣት ለምንድነው? ብዙ ብንሰበስብ ብዙ አንበላም፡፡ ብዙ ሰው ብናውቅም ብዙ ወዳጅ አይደለም፡፡ ብዙ ብንወልድም ጠቃሚው አንድ ነው፡፡ ብዙ ብናውቅም አንዱን ለመፈጸም ነው የምንታገለው፡፡ የሚያስፈልገው አንድ ወይም ጥቂት ነው፡፡

 ቤታችን ላስገባናቸው ወዳጆቻችንና የትዳር አጋሮቻችን ብዙ ለማቅረብ እንፈልጋለን፡፡ ወደ ቤታችን የመጡት ግን በመጀመሪያ እኛን ለማግኘት ነው፡፡ እኛን የሚተካ፣ ፍቅራችንን የሚበልጥ ግብዣ የለም፡፡ ጥቂቱ ነገር በፍቅር ብዙ ነው፡፡ እኛ ግን የምንታወከው በብዙ ነው፡፡ ላስደስት ስንል እንደክማለን፡፡ ስንደሰት ግን እናስደስታለን፡፡

 ልብ አድርጉ! ጌታ ማርታን አልነቀፈም፡፡ የማርታ አገልግሎትም ያስፈልጋል፡፡ ማዕድ ግን ሁሉን አይተካም፡፡ ለአገልጋዮች ጠብ እርግፍ የሚሉ ቃሉን ግን መስማት አይችሉም፡፡ ቤታቸውን ለእግዚአብሔር ሰዎች ለቀዋል በዚህ ብቻም ረክተው ተቀምጠዋል፡፡“ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም” ያ መልካም ዕድል ከጌታ እግር ሥር ተቀምጦ ቃሉን መማር ነው፡፡ ዕድል ሁሉ ፈልጎን የሚመጣ ነው፣ ይህኛው ዕድል ግን የምንመርጠው ነው፡፡ በዓለም ላይ ካሉት ድንቅ ገጠመኞች አንዱ ቃሉን ማግኘት ነው፡፡ አንዳንድ ጸጋዎች ይወሰዳሉ፡፡ ሰውዬው ስለ በደለ ሳይሆን ጊዜ አላቸው፡፡ “ትንቢት ቢሆን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ” ይላልና /1ቆሮ. 13፡8/፡፡ ቃሉን የመስማት ዕድል ግን ለሚያከበሩት የማይወሰድ ዕድል ነው፡፡ እኛስ ይህንን ዕድል መርጠናል ወይስ በአጋጣሚ ነው ቃሉን የምንሰማው? በቤታችንስ ቃሉን እንሰማለን? ቃሉንስ እንደ ትልቅ ዕድል ቆጥረነዋል? በክብሩ እንድንይዘው እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

Monday, January 11, 2016

❖ ብዙ ሃይል፦

❖ ብዙ ኃይል
‹‹በጻድቅ ሰው ቤት ብዙ ኃይል አለ፤ የኃጥእ ሰው መዝገብ ግን ሁከት ነው።››
(ምሳ. 15÷6)፡፡

         በሰው ልጆች አኗኗር ውስጥ ኃይል እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ በኃይል እጦትና እጥረት ሰዎች ያለ መብራት በጨለማ ይሄዳሉ፤ ያልበሰለ በጥሬው ይበላሉ፡፡ ሰዎች በአቅም ማነስ ምክንያት ለተግባር ብዙ ይቸገራሉ፡፡ ኃይል የማይገባበት የኑሮ ክፍል የለም፡፡ ብዙ ነገሮች በብዙ ኃይል ጭምር የሚተገበሩ ናቸው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ በመንፈሳዊው ዓለም ስላለው ከፍተኛ ኃይል ይነግረናል፡፡ ጠቢቡ በዘመኑ ያስተዋለውን ባካፈለበት በዚህ ክፍል ላይ ጻድቅ ቤት ውስጥ ብዙ ኃይል እንዳለ ሲነግረን፤ በኃጢአተኛ መዝገብ ውስጥ ግን ሁከት አለ ይለናል፡፡

        ጠቢቡ ጻድቅና ኃጥእን፤ ቤትና መዝገብን፤ ኃይልና ሁከትን እነዚህን ሁለት ነገሮች ከሰው አንፃር በንጽጽር አቅርቦልናል፡፡ 
ጽድቅ የሚለው አገላለጽ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነትን ያገኘ እውነተኛ ማንነትን ሲያሳይ፤ 
ኃጥእ የሚለው አገላለጽ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ጸብ ውስጥ ያለና መንገድ የሳተ  ማንነትን ያመላክተናል፡፡ ቤት ልንኖርበትና ልንጠለልበት ያለንበትን ክልል ሲያሳይ፤ መዝገብ አንድ ሰው የሚሰበስበውን የሚያኖርበትን ስፍራ ያመለክተናል፡፡ ብዙ ኃይል የሚለው አገላለጽ ጽድቅ የሚለውን አዎንታዊ ቃል ተከትሎ የመጣ እንደ መሆኑ በዚያው መንገድ የምንመለከተው ብርቱ ነገር ሲሆን፤ ሁከት ደግሞ የደፈረሰ ያልጠራ፤ ሰላም የሌለበትን ነገር ያስረዳናል፡፡

    በቀደመው ኪዳን ‹‹ጽድቅና ኃጢአት›› መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ የምናስተውልበት፤ ውጤቱንም በግልጥ የምናይበት ሆኖ ከቀረበልን ነገር ዋናው ‹‹ኃይል›› ነው፡፡ ምድሪቱ ላይ ሰዎች በብዙ ነገራቸው ላይ ኃይልን አብዝተው ይሻሉ፡፡ አቅም ያጣንባቸው ነገሮች ሁሉ አንዳች ኃይልን ለመናፈቅ በቂ ምክንያት ነው፡፡ በዙሪያችን ብዙ የአቅም ማነሶችን እናስተውላለን፡፡ በጤና በኩል፤ በመብል በኩል፤ በሰላም በኩል፤ በደስታ በኩል ወገኖች በጥያቄ ተሞልተው ልብ እንላለን፡፡ ሰዎች መፍትሔን ይሻሉ፡፡ በሰለለና በዛለባቸው ነገር ላይም ምላሽን ይናፍቃሉ፡፡

        በምንኖርበት ዓለምና በሥጋ ለባሽ ላይ ሰዎች መደገፋቸው፤ የሚያልፈውንም ክንድ ማድረጋቸው ከሥጋት ወደ በለጠ ፍርሃት ውስጥ እየጨመራቸው ተጨንቀዋል፡፡ ዳሩ ግን በመዝሙር እንዲህ ተጽፎአል፤ ‹‹እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት። ሥራህ ግሩም ነው፤ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ።›› /መዝ. 65÷3/፡፡ ቀና ብልን የምናየው ሰማይ፤ ዝቅ ብለን የረገጥነው ምድር እንደ መጎናጸፊያ እስኪጠቀለል ድረስ ጠላት ዲያቢሎስና መልእክተኞቹ የሚዋሹበት ብዙ ኃይል አለ፡፡ እግዚአብሔር ብዙ ኃይል ነው፡፡ በሌላ ስፍራ መዝሙረኛው ‹‹ኃይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፤ እርሱም መድኃኒት ሆነልኝ›› /መዝ 117፣14/ ይላል፡፡ ተወዳጆች ሆይ፤ የእልልታና የመድኃኒት ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው፡፡

        እግዚአብሔር ያለን ብዙ ኃይል ነው፡፡ ምድሪቱ ላይ ብዙ ገንዘብ፤ ብዙ ሥልጣን፤ ብዙ እውቀት፤ ብዙ ጦር፤ ብዙ ብልሃት እንዳላቸው የምናስባቸው ሁሉ ከኃይለኛው አምላካችን፤ ከእግዚአብሔር ክንድ በታች ናቸው፡፡ ስለ አምላካችን ክንድ፡ ‹‹በክንድህ ብርታት እንደ ድንጋይ ዝም አሉ›› / ዘፀ 15፣16/ ተብሎ ተጽፍአል፡፡ ማን እንደ እግዚአብሔር?

       በጌታ የተወደዳችሁ፤ በውስጣችን ላለው ዝለት፤ በዙሪያችን ለምናስተውለው ተስፋ መቁረጥ ‹‹በጻድቅ ቤት›› የተባለውን ልብ በሉ፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኛችሁ፤ አብርሃም በጸደቀበት በዚያው መንገድ ጽድቅን ያገኛችሁ፤ ያላችሁን አስተውሉ፡፡ በእናንተ ዘንድ ብዙ ኃይል አለ፡፡ ችግርን አልፎ፤ መከራን አልፎ፤ ሀዘንን አልፎ፤ መለያየትን አልፎ፤ በሽታን አልፎ የሚሠራ ኃይል፤ ሁሉን ያደርግ ዘንድ ቻይ የሆነ አሳቡም ይከለከል ዘንድ ከቶ የማይቻል የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር ስሙ ብሩክ ይሁን፡፡ ሰዎች በእጃቸው ሥራ፤ በአስተሳሰባቸው ብልሃት፤ በወገናቸው ትጋት በሚደገፉበት በዚህ የዘመን ማብቂያ እናንተ በእግዚአብሔር መተማመንን ልማድ አድርጉ፡፡

        ሰይጣን ዛሬም ይዋሻል፡፡ የዘመን ርዝማኔ ትምህርት እንደማይሆን ከሰይጣን በላይ አብነት የለም፡፡ እርሱ ውሸትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል /ዮሐ 8፣44/፡፡ በእግዚአብሔር ብዙ ኃይል ላይ ጠላት የማይቋረጥ ዘመቻን ከፍቷል፡፡ መጽናናትን ከእግዚአብሔር ስትሹ፤ ዕረፍትን ከሕያው አምላክ ስትናፍቁ፤ የጉዳዮቻችሁን መከናወን፤ የጉድለቶቻችሁን ሙላት ስትጠባበቁ ጠላት ዲያብሎስ ‹‹አይችልም››ን ወደ ጆሮአችሁ ይዞ ይመጣል፡፡ እርሱ ጌታ ባለ ብዙ ኃይል ነው፡፡ የጻድቅ ቤት በዚህ የተሞላ ነው፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች የገዛ መንገዳቸው ያመጣውን ነገር ሳይሆን የእግዚአብሔርን ኃይልና ማዳን በኑሮአቸው የሚለማመዱ ናቸው፡፡

       እናንተ የምታምኑ ሆይ፤ በኃጥእ መዝገብ አትቅኑ፡፡ በዚህ የሠሩባት የማታ ማታ ሕይወትን ከስረዋልና፡፡ እግዚአብሔር የሁከት አምላክ አይደለም፡፡ የአመፀኞች መዝገብ ለዚህ ዓለም ስርዓትና መሻት እንደ ማጣፈጫ ቢሆንም፤ የክርስቶስ የሆኑቱ ከዚህ እድል ፈንታ የላቸውም፡፡ በእግዚአብሔር ጽድቅ ጥላ ስር የሆኑ ሁሉ ባለ ብዙ ኃይል ናቸው፡፡ እርሱም የዘላለም አምላክ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህንን ኃይል ከብዙ የኑሮአችን ክፍል ጋር አያይዘን ልናየው እንችላለን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ክንድ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ በሉዓላዊነት ሲገለጥ እናስተውላለን፡፡ እኔ ግን ለዚህ ዝግጅት ማየት የፈለኩት ከማዳኑ ጋር የተያያዘውን ነው፡፡

       ‹‹በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና›› /ሮሜ 1፣16/፡፡ እግዚአብሔር ኃይሉን ለማዳን መጠቀሙ ድንቅ ነው፡፡ በዙሪያችን ሰዎች በአቅማቸው ያላቸውን ነገር ለጥፋትና ለሌሎች ውድቀት ሲያውሉት ማየት ልብን ያሳዝናል፡፡ ለነገሩ ትንሽ ያላት እንቅልፍ የላትም አይደል ነገሩ፡፡ ከእግዚአብሔር አንፃር የዚህ ዓለም ቀዳሚ ባለጠጋም የተረቱ ሰለባ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይችላል፡፡ ተስፋችሁን ሊቀጥል፤ ከገባችሁበት መከራ ሊያወጣ ይችላል፡፡ የመረረባችሁን ሊያጣፍጠው፤ የጠመመባችሁን ሊያቀናው እርሱ ይችላል፡፡ ከሞትና ከሲዖል ኃይል የሚያድን ኃይል እርሱ ጌታ ነው፡፡ ሰዎች ባላቸው ብዙ ነገር ሊወጡ የማችሉት ብርቱ ጠላት ዲያቢሎስ የዚህ ዓለም ገዥ በሆነበት ሁኔታ፤ እግዚአብሔር ብቻ ያድናል፡፡

        ስለማናፍርበት ነገር ማውራት እንዴት ደስ ያሰኛል፡፡ ዓለሙ በብዙ የሚያሳፍር ወሬና የቅሌት ኑሮ የተጨናነቀ ነው፡፡ ወንጌላችን በዚህ የጨለማ ድቅድቅ መሐል ብርሃን፤ አልጫ በሆነው ነገር ላይ ጨው ነው፡፡ እናንተ እውነተኞች ሆይ፤ ከፀሐይ በታች የዚህ ዓለም ስርዓት ትኩረትና ከፍታ የሚሰጠው ነገር እናንተ ቤት የለ ይሆናል፡፡ ዳሩ ግን ልብ በሉ፤ ሰዎች ሁሉ የሚድኑበት፤ መቃብርን አልፈው ሕያው የሚሆኑበት፤ ከከንቱ ኑሮ የሚገላገሉበት፤ ከሞተ ሥራ ሕሊናቸው የሚነፃበት ኃይል በእናንተ ውስጥ አለ፡፡ ይህንን ብልሃት አያገኘውም፡፡ ሀብትና ንብረት አይገዛውም፡፡ ሥልጣንና ጉልበት አስሮ አያመጣውም፡፡ የልብ እምነት ግን ከዚህ ብዙ ኃይል ጋር ያስተሳስራል፡፡

       ወዳጆቼ፤ ይህንን ዓለም በምን ታሸንፉታላችሁ፡፡ ትብታብና ሰንሰለቱ፤ ጭፍራና ሠራዊቱ ርኩስ መንፈስ የሆነ፤ ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም የሚተጋውን ክፉ እንዴት ትሻገሩታላችሁ? እንዲህ ካለው ባላጋራ መዳን በሌላ በማንም የለም /ሐዋ 4፣12/፡፡ ‹‹እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥ ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።›› (1 ቆሮ. 1÷23-24)፡፡

                 ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!