Friday, April 22, 2016

❖የሺህ ዓመት መንግሥት

የሺህ ዓመት መንግሥት ምን ማለት ነው?፣ እሱንስ በጥሬው መረዳት ይገባል?
 የሺሀ ዓመቱ መንግሥት ርዕስ የተሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለሚገዛበት 1000 ዓመት ነው። አንዳንዶች 1000 ዓመትን በተምሳሌታዊ ዘይቤ ሊተረጉሙ ይሻሉ። አንዳንዶች 1000 ዓመቱን የሚረዱት ባመዛኙ ዘይቤአዊ አባባል ነው፣ረጅም የሆነ ጊዜ፣በጥሬው ያልሆነ፣ በሥጋ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ እንደሚገዛ ያለ። ሆኖም፣ ራዕይ 202-7 ላይ፣ ስድስት ጊዜ የሺ ዓመቱ መንግሥት ተለይቶ 1000 ዓመት እንደሚሆን ተገልጿል። እግዚአብሔርረጅም የሆነ ጊዜየሚለውን ለማሳየት ቢፈልግ፣ በቀላሉ ሊያደርገው ይችል ነበር፣ ለይቶ እና ደጋግሞ ትክክለኛውን የጊዜ ቅንብብ ከመንገር ይልቅ።
መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ሲመለስ በኢየሩሳሌም እንደሚነግሥ ነው፣ በዳዊትም ዙፋን ላይ ይቀመጣል (ሉቃስ 132-33) ሁኔታዊ ያልሆኑት ኪዳናትም በጥሬው የሆነ፣ የክርስቶስ ሥጋዊ መመለስን ያሳያል፣ መንግሥቱን ለማቋቋም። አብርሃማዊው ኪዳን ለእስራኤል ምድርን ተስፋ ሰጥቷል፣ መጪውን ትውልድና ገዥነት፣ እና መንፈሳዊ ባርኮት (ዘፍጥረት 121-3) የፍልስጥኤም ኪዳን ለእስራኤል ተስፋ ሰጥቷል፣ ወደ ምድሩ መመለስና ምድሩን መሙላት (ዘዳግም 301-10) ዳዊታዊው ኪዳን ለእስራኤል ይቅርታን ተስፋ ሰጥቷልማለትም አሕዛብ የሚባረኩበት አግባብ (ኤርምያስ 3131-34)

በዳግም ምጽአቱ፣ እነዚህ ኪዳናት ተፈጻሚ ይሆናሉ፣ እስራኤል ከሕዝቦች ሁሉ ሲሰባሰብ (ማቴዎስ 2431) የተለወጡት (ዘካርያስ 1210-14) እና ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፣ በመሲሑ በኢየሱስ ክርስቶስ መሪነት። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሊኒየሙ ጊዜ ሁኔታን ይገልጻል፣ ፍጹም የሆነ አካባቢ በሥጋዊና በመንፈሳዊ ረገድ እንደሚሆን። የሰላም ጊዜ ይሆናል (ሚኪያስ 4:2-4 ኢሳይያስ 32:17-18) ደስታ (ኢሳይያስ 61:7 10) ምቹ (ኢሳይያስ 40:1-2) ምንም ድህነትና ሕመም አይኖርም (አሞጽ 9:13-15 ኢዩኤል 2:28-29) መጽሐፍ ቅዱስ ጨምሮ አማኞች ብቻ ወደ ሚሊኒየሙ መንግሥት እንደሚገቡ ይነግረናል። በዚህም ምክንያት፣ ፍጹም የጽድቅ ሰዓት ይሆናል (ማቴዎስ 25:37 መዝሙር 24:3-4) ታዛዥነት (ኤርምያስ 3133) ቅድስና (ኢሳይያስ 358) እውነት (ኢሳይያስ 6516) እና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (ኢዩኤል 228-29) ክርስቶስ እንደ ንጉሥ ይገዛል (ኢሳይያስ 9:3-7 11:1-10) ከዳዊት ጋር እንደ ገዥ (ኤርምያስ 33:15-21 አሞጽ 9:11) የከበሩና ገዥዎችም ደግሞ ይገዛሉ (ኢሳይያስ 32:1 ማቴዎስ 19:28) ኢየሩሳሌምም የፖለቲካ ማዕከል ትሆናለች (ዘካርያስ 8:3)

ራዕይ 202-7 የሚሊኒየሙን መንግሥት ትክክለኛ ሰዓት ያሳያል። ከእነዚህ ቃሎች ውጭም፣ በርካታ ሌሎች የመሲሑን በምድር ላይ መንገሥ የሚያመለክቱ በጥሬው የተቀመጡ አሉ። አብዛኞቹ የእግዚአብሔር ኪዳናትና ተስፋ ፍጻሜዎች በጥሬው፣ በአካላዊ፣ በመጪው መንግሥት ላይ ያርፋል። የሚሊኒየሙን መንግሥት እና የሱም 1000 ዓመት ጊዜ መሆን የሚለውን ጥሬ ትርጉም ላለመቀበል የሚያስችል ምንም ዓይነት ተጨባጭ መሠረት የለም።


Tuesday, April 12, 2016

❖መነጠቅ መቼ ነው የሚሆነው?



መነጠቅ መቼ ነው የሚሆነው?

የመነጠቅ ጊዜ ጉዳይ ከታላቁ መከራ ጋር በተያያዘ አንደኛው እጅግ አወዛጋቢው ጉዳይ ነው፣ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን። ሦስቱ ዋነኛ አመለካከቶች ቅድመ-ታላቁ መከራ (ከታላቁ መከራ በፊት የሚሆን መነጠቅ)፣ ማዕከላዊ ታላቁ መከራ (በታላቁ መከራ መሀከል ወይም በዚያ አካባቢ የሚሆን ታላቁ መከራ)፣ እና ድኅረ-ታላቁ መከራ (በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ የሚሆን መነጠቅ) ናቸው። አራተኛው አመለካከት፣ ከቁጣ-በፊት በሚል ይታወቃል፣ ይህም ከማዕከላዊ ታላቁ መከራ አቋም መጠነኛ ማሻሻያ ያለው ነው።
በመጀመሪያ፣ የመከራውን ዓላማ መገንዘብ ጠቃሚ ነው። እንደ ዳንኤል 9፡27 ሱባዔ “ሰባት” (ሰባት ዓመት) አለ፣ ይህም ገና የሚመጣ ነው። የዳንኤል አጠቃላይ ትንቢት፣ የሰባ ሰባቶች (ዳንኤል 9፡20-27) የሚናገረው ስለ እስራኤል ሕዝብ ነው። እሱም፣ እግዚአብሔር አትኩሮቱን በተለይ በእስራኤል ላይ የሚያደርግበት ጊዜ ነው። የሰባት ሱባኤ መከራ የግድ መሆን ያለበት እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር በተለይ የሚያደርገው ነው። ይህም ማለት ቤተ ክርስቲያን አትኖርም ማለትን አያመለክትም፣ ቤተ ክርስቲያን በዛን ሰዓት በምድር ላይ ለመኖሯ ጥያቄ ያስነሣል እንጂ።
ቀዳሚው የመነጠቅ ምንባብ በቅዱስ ቃሉ ውስጥ 1 ተሰሎንቄ 4፡13-18 ነው። እሱም የሚያስረግጠው በሕይወት ያሉት አማኞች ሁሉ፣ ከሞቱት አማኞች ጋር፣ ጌታ ኢየሱስን በአየር እንደሚቀበሉትና ለዘላለም ከእሱ ጋር እንደሚሆኑ ነው። መነጠቅ እግዚአብሔር የራሱን ሕዝብ ከምድር ላይ የሚወስድበት ነው። ከጥቂት ቁጥሮች በኋላ፣ በ1 ተሰሎንቄ 5፡9፣ ጳውሎስ ይላል፣ “እግዚአብሔር ለቁጣ አልመረጠንምና፣ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደኅንነትን ለመቀበል እንጂ።” የራዕይ መጽሐፍ በቀዳሚነት ስለ ታላቁ መከራ ጊዜና ሰዓት በቀዳሚነት የተናገረ፣ ትንቢታዊ መልእክት ነው፣ እግዚአብሔር ቁጣውን በምድር ላይ እንዴት እንደሚያፈስ፣ በታላቁ መከራ ጊዜ። እሱም የማይጣጣም ይመስላል፣ እግዚአብሔር አማኞች ቁጣውን እንደማይቀበሉና ቀጥሎም በታላቁ መከራ ይሣቀዩ ዘንድ በምድር ላይ የሚተዋቸው። ሐቁ፣ እግዚአብሔር ክርስቲያኖችን ከቁጣ ለማዳን የሰጠው ተስፋ ባጭሩ የራሱን ሕዝብ ከምድር ላይ ለመውሰድ ቃል የገባው እነዚያን ሁለት ሁነቶች አያይዞ ለማስኬድ ይሆናል።
ሌለኛው የመነጠቅ ጊዜ ወሳኝ አንቀጽ ራዕይ 3፡10 ነው፣ ይሄውም ክርስቶስ አማኞችን “ከፈተና ሰዓት” ሊያድናቸው ቃል የገባበት፣ በምድር ላይ ሊሆን ካለው። ይህ ሊሆን የሚችለው ሁለት ነገሮች ነው። አንድም፣ ክርስቶስ አማኞችን በፈተና መሐል ሊጠብቃቸው መቻሉን፣ ወይም አማኞችን ከፈተና መሐል ሊያወጣ መቻሉን ነው። ሁለቱም ሁነኛ ትርጉም ይኖራቸዋል፣ ከግሪኩ ቃል ትርጉም “ከ” የተነሣ። ሆኖም፣ አማኞች ከምን እንደሚጠበቁ ተስፋ እንደተሰጠ መገንዘብ ጠቃሚ ነው። እሱ ፈተና ብቻ አይደለም፣ ግን የፈተና “ሰዓት” ነው። ክርስቶስ አማኞችን ሊጠብቅ ቃል ገብቷል፣ ፈተና ካለባቸው ሁነኛ ጊዜና ሰዓት፣ እሱም ታላቁ መከራ ተብሎ የሚታወቀው። የታላቁ መከራ ዓላማ፣ የመነጠቅ ዓላማ፣ የ1 ተሰሎንቄ 5፡9 ፍቺ፣ እና የራዕይ 3፡10 ትርጓሜ ሁሉ ግልጽ የሆነ ድጋፋቸውን የሚሰጡት ለቅድመ-ታላቁ መከራ አቋም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በጥሬውና በቋሚነት ከተተረጎመ፣ ቅድመ-ታላቁ መከራ አቋም እጅግ የተሻለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው ትርጓሜ ነው።

❖የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ምንድነው?

የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ምንድነው?

“መነጠቅ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም። ቢሆንም፣ የመነጠቅ ጽንሰ-ሐሳብ በቅዱስ ቃሉ በግልጽ ተስተምሯል። የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ፣ እግዚአብሔር ሁሉንም አማኞች ከምድር ላይ የሚወስድበት ሁነት ነው፣ የጽድቅ ፍርዱን በምድር ላይ ከማፍሰሱ በፊት መንገዱን የሚያመቻችበት፣ በታላቁ መከራ ጊዜ። መነጠቅ በቅድሚያ የተገለጸው በ1 ተሰሎንቄ 4:13-18 እና 1 ቆሮንቶስ 15:50-54 ላይ ነው። እግዚአብሔር የሞቱትን አማኞች ሁሉ ያስነሣቸዋል፣ የከበረ አካልም ያለብሳቸዋል፣ ከምድርም ይወስዳቸዋል፣ በሕይወት ካሉት አማኞች ጋር፣ እነሱም ደግሞ በዛን ጊዜ የከበረ አካል የሚሰጣቸው። “ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን” (1 ተሰሎንቄ 4፡16-17)።
መነጠቅ በባሕርዩ ቅጽበታዊ ይሆናል፣ በዛን ሰዓትም የከበረውን አካል እንቀበላለን። “እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን” (1 ቆሮንቶስ 15፡51-52)። መነጠቅ ሁላችንም በተስፋ መጠበቅ የሚኖርብን የከበረ ሁነት ነው። በመጨረሻም ከኃጢአት ነጻ እንወጣለን። ከእግዚአብሔር መገኘት ጋር ለዘላለም እንሆናለን። እጅግ በርካታ ክርክሮች ከመነጠቅ ፍቺ እና ከስፋቱ አኳያ ተካሂደዋል። ይህ የእግዚአብሔር ሐሳብ አይደለም። ይልቁንም፣ መነጠቅን በተመለከተ፣ እግዚአብሔር “እርስ በርሳችን በዚህ ቃል እንድንጽናና” ይፈልጋል፣ (1 ተሰሎንቄ 4፡18)።
                                                       ክብር ለእግዚአብሄር ይሁን