የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች፦
ምዕራፍ ዐሥራ ሦስት
v የክርስቲያን ኑሮ በእግዚአብሔር ዘንድ
ምን መምሰል እንዳለበት በምዕራፍ 12 ተመልክተናል:: አሁን ደግሞ ያ በመልካምነት በእግዚአብሔር ፊት እንዲገለጥ የተገባው የክርስቲያን
ሕይወት በምድራዊ መንግሥት ዘንድ እንዴት መገለጥ እንዳለበት በዚህ ምዕራፍ እንመለከታለን::
Ø ክርስቲያን :
·
ከዚህ ዓለም ያልሆነ፤
·
ሀገሩም በሰማይ የሆነ /ሰማያዊ/ ዜግነት ያለው፤
·
የሚያገለግለውም ንጉሥ ክርስቶስ ኢየሱስ የሆነለት ነው:: (ዮሐ 15፥19፤ 17፥14-16፤
ፊል 3፥20፤ ቈላ 3፥24)
Ø ይሁን እንጂ :-
·
በዚህ ምድራዊ ኑሮ እያለ የዚህ ምድር መንግሥት አገልጋይ (ሠራተኛ)፤
·
የምድሪቱም መንግሥት ታማኝ ዜጋ እንደሆነ ሊገነዘብ ይገባል::
Ø ስለዚህም:- ክርስቲያን በዚህ ዓለም
ኑሮው ታማኝነት እና መልካም አኗኗር ምን እንደሆነ ለሌላው የሚያስተምርበት ኑሮ ሊኖረው ይገባል ማለት ነው::
v ቁጥር 1-7 :-
Ø በዚህ ክፍል የሚያስረዳው :-
·
ሥልጣን ሁሉ የእግዚአብሔር እንደሆነ (13፥1)
·
ክርስቲያንም በታማኝ ኑሮው ለባለሥልጣናቱ ይታዘዝና ይገዛ ዘንድ ተገቢ እንደሆነ (1ጴጥ 2፥13-17)
·
የመግዛቱ ሥርዓት የእግዚአብሔር ሥርዓት እንደሆነ የሚያሳይ ነው::
Ø ይህ ማለት ክርስቲያን የሚቃወመው ምድራዊ
መንግሥት የለም ማለት ግን አይደለም
·
የተሠራለትን ዓላማ የሚያደናቅፍ ማለት የሚኖርለትን እውቀት የሚቃወም ትዕዛዝ ከባለሥልጣናቱ
ቢመጣ ይሁን ብሎ የሚጓዝ ማለት ግን አይደለም:: ከእውነት የወጣን ትዕዛዝ ሊቃወም ግድ አለበት:: (ሐዋ 4፥18-20 ፤ 5፥28-29
፤ 5፥40-42)
Ø ይሁን እንጂ ተቃውሞውን የሚገልጥበት
መንገድም ሆነ ክፋቱን የሚዋጋበት መሣሪያ ሥጋዊ አይደለም
·
2ቆሮ 10፥3-5 ፤ ማቴ
10፥28)
v ቁጥር 8-10 :-
Ø እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም
ዕዳ አይኑርባችሁ
·
ይህ ቃል የዚህ ክፍል መሪ ቃል ነው፤
·
ከላይ በቁጥር 7 ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ ብሎ ነበርና አሁን ባለዕዳ አትሁኑ በማለት ያንን
ምክር ያፀናል::
Ø ልናስተውል የሚገባን ሐዋርያው ስለ ገንዘብ
ዕዳ ብቻ እያወራ እንዳልሆነ ነው፤
·
ጳውሎስ ራሱ “ዕዳ አለብኝ” ብሎ ነበር (ምዕ 1፥14)
·
ይህም ዕዳ የእውነት ቃልን ያለማድረስ ዕዳ ነውና ሊከፍል ወይም ሊወጣው ይተጋል (ምዕ 1፥10፤
15)
·
ዕዳ ማለት ከእኛ የሚፈለግ ነገር ከሆነ ኃጢአተኛው ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ አለማስተማር ከእኛ
የሚፈለግ ዕዳ ተሸካሚዎች ያደርገናል ማለት ነው:: (ሕዝ 33፥6፤ 34፥1-10)::
v ቁጥር 11-14 :-
Ø ሐዋርያው ከላይ የተመለከትናቸውን ትዕዛዛት
ሁሉ የሰጠበትን ምክንያት በእነዚህ ከ 11-14 ካሉት ቁጥሮች ይገልጥልናል::
Ø እርሱም :-
·
የመዳናችን መቅረብ ፣ ይህም ታማኝ ሠራተኛ የሚሸለምበት ጊዜ (ማቴ 25፥5-6)፤
·
ማታለል፣ ዐመፅ እና ውሸት የጨለማ ሥራ ስለሆነና ከእኛ መወገድ ስላለበት (ቁጥር 12)፤
·
የብርሃንን ጋሻ ጦር ልንለብስ ስለሚገባ፣ ያውም የጠላትን ኃይል የምንዋጋበት (ኤፌ 6፥10-18)
·
ከሥጋ ሥራዎች ተለይተን በአግባብ መመላለስ (13፥13)
ማስገንዘቢያ :-
Ø በዚህ ምዕራፍ 13፥13 ላይ ተዘርዝረው
የቀረቡት ስድስት ኃጢአቶች ሲሆኑ እነርሱም የዘመኑ ኃጢአቶች ናቸው::
Ø ምክንያቱም : በቁጥር 11 ላይ “ዘመኑን
እወቁ” ካለ በኋላ በ ቁጥር 12 ላይ ደግሞ “ቀኑ ቀርቧል” በማለት አሳስቧልና ነው::
Ø እነዚህ በቁጥር 13 ላይ የቀረቡት የመጨረሻው
ዘመን ጉልህ ኃጢአቶች :
·
ዘፈንና ስካር
·
ዝሙትና መዳራት
·
ክርክርና ቅናት ናቸው
No comments:
Post a Comment