❖ መንፈስ ቅዱስን ማወቅ፦
" ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፣ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለሆነ ሊቀበለው
የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር እናንተ ታውቃላችሁ "
(ዮሐ 14: 15 -17)።
መንፈስ ቅዱስን ማወቅ ማለት ከሦስቱ አካላት አንዱ መሆኑን ወይም ከአብና ከወልድ ጋር በመከኮታዊነት ማንነቱ የተስተካከለ፣ እና ግብሩን ማወቅ ማለት ብቻ አይደለም ።
መንፈስ ቅዱስን ማወቅ ማለት በእኛ በክርስቲያኖች ሕይወት መዳናችን እንዲፈጸም ያለውንም ጥልቅ ሚና መረዳት ማለትም ነው።
በሐዋርያትት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ እንደምናነበው በኤፌሶን ይኖሩ የነበሩ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አዳኝነት አምነው ደቀመዛሙርት የተባሉ። አንዳንዶችን ቅዱስ ዻውሎስ አግኝቶ ስለ መንፈስ ቅዱስን ማግኘት ሲጠይቃቸው የመለሱለት መልስ ይህንኑ ያስረዳል " እነርሱም መንፈስ ቅዱሰ እንዳለ ስንኳ አልሰማንም አሉት " ( ሐዋ 19: 2 -3) እነዚህ ሰዎች የማያምኑ ሆነው አይደለም ይሁን እንጂ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታቸው በሙላት በመገለጥ ማየት ያለባቸውን የመንፈስ ፍሬና የእግዚአብሔርን ክብር አላዩ ም።
የሚያምን ሰው ልብ ውስጥ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ስለሚኖር ( ዮሐ 7:35) መንፈሳዊ ፍሬዎችም ሊገለጡ ይገባል። ዘር የሚተካው ፣ የሚያበቅለውም ራሱን ነው። የስንዴ ዘር የስንዴ ፍሬን ነው የሚሰጠን ። መንፈስ ቅዱስም በውስጣችን ንጹሕ ዘር ስለሆነ የሚሰጠን ፍሬዎችን ስናጠና ፍቅር ፣ደስታ፣ ሰላም፣ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት ፣ እምነት፣ የዋህት ፣ራስን መግዛትን ነው። ( ገላ 5:22) ስለዚህ በውስጣችን የሚኖረውን መንፈስ ቅዱስን ማወቅ እንድናከብረው ብቻ ሳይሆን በሥጋ ሥራ እንዳናሳዝነውም ይጠቅመናል።
( ኤፌ 4: 30)
መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያን ህይወት ውስጥ ያለውን መጠነ ሠፊ ጥቅምንም ይዘረዝራል
ከእነዚህም ውስጥ፦
☞ወደ እውነት ሁሉ ይመራል ዮሐ 16:13።
☞ስለ ኃጢአት ይወቅሳል ዮሐ 16:8።
☞ስጦታን ያፈስሳል ሐዋ 2:38 ፣ ሐዋ 10: 4 - 5።
☞ፍጹም ደስታን ይሰጣል ዮሐ 16:20።
☞ኃይልን ይሰጣል ሮሜ 15:18።
☞ምሥጢር ይገልጣል 2ኛ ቆሮ 2:10 - 11፣ 1ኛ ተሰ 1:5።
☞ ድካማችንን ያግዛል ሮሜ 8:26።
☞ያጥባል፣ ይቀድሳል፣ ያጸድቃል 1ኛ ቆሮ 6:11።
☞በኢየሱስ ክርስቶስም ስም በግልጥ ለመመስከር አቅምንና መንፈሳዊ ጉልበትን ይሰጣል
(ሐዋ 4: 24 – 31)።

No comments:
Post a Comment