በእኛ ውስጥ ያለው መንፈስ ቅዱስ ከአብ ና ከወልድ ጋር ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያንን ከአካሏ ከክርስቶስ እንዲሁም በተለያዩ የምድር ስፍራ ካሉት ከምናውቃቸውም ከማናውቃቸውም አማኞች ጋር በሕይወት እንድንተሳሰር አድርጎናል።
መጽሐፍ ቅዱስ አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል እንዲል፤ (1ቆሮ 12:13።)
ከዚህ መንፈስ ቅዱስ የተነሳ እኛ በአብና በወልድ ውስጥ እንዲሁ አብና ወልድም በእኛ ውስጥ ለመሆን ችለዋል። "ከመንፈሱ ስለ ሰጠን፥ በእርሱ እንድንኖር እርሱም በእኛ እንዲኖር በዚህ እናውቃለን"። (1ዮሐ 4:13።)
የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ውስጥ ከመሆኑ የተነሳ የክርስቶስ ወገን ሁነናል። (ሮሜ 8:9።) ይሁን እንጅ ይህ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ውስጥ ሁኖ ዝም ብሎ መቀመጥ ሳይህን የሚሠራው ሥራ የሚገልጠው ነገር አለ።
የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ውስጥ ከመሆኑ የተነሳ የክርስቶስ ወገን ሁነናል። (ሮሜ 8:9።) ይሁን እንጅ ይህ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ውስጥ ሁኖ ዝም ብሎ መቀመጥ ሳይህን የሚሠራው ሥራ የሚገልጠው ነገር አለ።
መንፈስ ቅዱስ በእኛ ሕይወት የሚገልጠው በልጁ የተገለጠውን የአብን ፍቅር ወይም ልጁን ኢየሱስን ነው። "በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። (ሮሜ 5:5 )
እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና። ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ፡— ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ።" (ዮሐ 16:13-15)
መንፈስ ቅዱስ በእኛ ሕይወት የሚገልጠው የዘላለም ሕይወትን ነው። የሰማዩን መንግሥት ነው። የማያልፈውን ነው። በአጠቃላይ መንፈስ ቅዱስ የሚገልጠው ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው እርሱ ሲገለጥ ደግሞ በርግጥም አብም ይገለጣል። መንፈስ ቅዱስ አብን ይገልጣል ስንል የአብን የዘላለም ሐሳብ ማለት ነው። ይኼም ሐሳቡ በልጁ የመስቀል ስራ የጀመረው፤ መንፈሱን በመላክ እየሠራ ያለው እንዲሁም በልጁ ዳግመኛ መገለጥ የሚጠቀልለውን የዘላለሙን ሐሰብ ማለት ነው።

No comments:
Post a Comment