በግሪክኛ ቋንቋ ቤተክርስቲያን"አቅሌስያ"ተብላ ተጠርታለች።ትርጉሙም"የተጠሩ "ማለት ነው።ይህንን ትርጉም በተለያዩ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በተለይም በቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት እናገኘዋለን፦
" በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት፥ የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት፤"
(1ኛ ወደ ቆሮ1:2)።
ኢየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያ አስራ ሁለት ቅዱሳን ሐዋርያትን ጠራ።ከእነዚህ ጋር የተጠሩ 36 ቅዱሳት አንስትን ጨምሮ 72 አርድእት ነበሩ።ኢየሱስ ክርስቶስ በእነዚህ ቤተክርስቲያንን መሠረተ።
ቤተ ክርስቲያን በምድር ያለች የእግዚአብሔር ተቋም ናት። የተመሠረተችውም ለአንድ ዓላማ ነው።የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ለመሆን ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደሰማይ ከማረጉ በፊት ደቀመዛሙርቱን እንዲህ ብሎአል፦
ቤተ ክርስቲያን በምድር ያለች የእግዚአብሔር ተቋም ናት። የተመሠረተችውም ለአንድ ዓላማ ነው።የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ለመሆን ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የምድር አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደሰማይ ከማረጉ በፊት ደቀመዛሙርቱን እንዲህ ብሎአል፦
"ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።" (የሐዋ ሥራ 1:8)።
ይህ ዓላማ ቤተክርስቲያን ለምን እዚህ ምድር ላይ እንደምትኖር በሚገባ ያሳያል። የቤተክርስቲያን ሠሪዋም መሠረቷም እንዲሁም ማእዘንዋም ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"አንተ ዓለት ነህ ዓለት የተባለ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ የመሰከረው መስክርነት ነው። በአንተ ዓለትነት ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።" (የማቴ 16:18)"
ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"
(1ኛ ቆሮ 3:11)
"በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ፤፤(ኤፌ2:20)።
ቤተክርስቲያን እስከ አሁን ድረስ በነቢያትና ሐዋርያት ትሠራለች፤ ሠራተኞችም ነቢያትና ሐዋርያት ናቸው። ነገር ግን እያንዳንዱ እንዴት እንደሚሠራ መጠንቀቅ ይኖርበታል።
" የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ።"(1ኛ ቆሮ 3:10)።
ቤተክርስቲያንን ለማነጽ የሁሉም የቤተክርስቲያን አካል ደርሻ ነው። ነገር ግን በፊተ አውራሪነት የሚመግቡ መሪዎች አሉ።" እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።"(1ኛ ቆሮ 12:28)።
እነዚህ ሁሉ ቤተክርስቲያንን ለማነጽ ሥራ ሥራቸውን መሥራት አለበቸው።" አጵሎስ እንግዲህ ምንድር ነው? ጳውሎስስ ምንድር ነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደ ሰጣቸው ያገለግላሉ።" (1ኛቆሮ3:5)
ቤተክርስቲያንና ዓላማዋ፦
እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። (ማቴ 28፥19-20 ) ይህ ካልሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተክርስቲያንና ከአገለጋዮቹ ጋር አይኖርም
2. ለእግዚአብሔር ቃልና ለክርስቲያናዊ ስነምግባር ግዴለሽ አለመሆን፦
በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው። (ራዕ 3፥16 ) ይህ ደንታ ቢስነት ቤተክርስቲያንን አለማዊ ያደርጋታል .ከእግዚአብሔር መንግሥትም ያወጣታል ቤተክርስቲያን በምድር ያለሽ የእግዚአብሔር መንግሥት ናትና
3. በምድር የምታበራ መቅረዝ ናት፦
በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰው ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር። (ራዕ 1፥13) መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ። የቤተክርስቲያን መኖር በጨለማው ዓለም እንድታበራ ነው የተቃጠለ አንቦል ለምንም አይጠቅም ። ቤተክርስቲያን የክርስቶስን ብርሃን ያለማቋረጥ ማብራት ይኖርባታል
4. የዲብሎስን ሥራ ማፍርስ፦
ይህም ዘርኘነት፤ ጥላቻ፤ ርኩሰት በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር ቅዱስ ባህርይ የማይሠማሙትን ሁሉ ማስወገድ ዓላማዋና ተልኮዋ ነው።
ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም። (1ኛ ዮሐ 3፥9)
ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም። (1ኛ ዮሐ 3፥9)
5. ፍቅርን መግለጽ፦
ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና። ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም። ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል። እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል። (1ኛ ዮሐ 4 ፡7-12)
ፍቅር የሌላት ቤትክርስቲያንና ፍቅር የሌለው ክርስቲያን እግዚአብሔር በውስጡ የለም ያለፍቅር ክርስትና የለም።
No comments:
Post a Comment