አለማወቅ የደገሰው ሞት
እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን አለማወቅ የጥፋት ሁሉ ምንጭ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ "ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ" ሆሴዕ 4:6 ሰው የሳተው ትልቅ እውቅት ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
በአዲስ ኪዳን ደግሞ ጳውሎስ እግዚአብሔርን ለማወቅ አለመፈለግ ወደ ሞት እንደሚያደርስ ተናግሯል፡፡ “እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ዓመፃ ሁሉ፥ ግፍ፥ መመኘት፥ ክፋት ሞላባቸው፤ ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን፥ ክርክርን፥ ተንኰልን፥ ክፉ ጠባይን ተሞሉ፤ የሚያሾከሹኩ፥ ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚያንገላቱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያስተውሉ፥ ውል የሚያፈርሱ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት ያጡ ናቸው፤ እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም።” ሮሜ 1፡28-32 እነዚህ የተዘረዘሩት 21 ነውሮች እግዚአብሔርን ለማወቅ ባለመውደድ ለማይረባ አእምሮ በተሰጡ ሰዎች የተሠሩ ናቸው፡፡ወገኖቼ እውቀትን መጥላት የለብንም፡፡ እውቀት ካጣን እንጠፋለን፡፡ በተለይ እግዚአብሔርን ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ውስጣችን እግዚአብሔርን ይጠማ፤ ፊቱን እንፈልግ፤ ሳንፈልገው የፈለገንን አምላክ እንፈልገው፡፡
ወስብሀት ለእግዚአብሔር!!!
No comments:
Post a Comment